የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደሴ ዲስትሪክት ንብረት በግልጽ ሐራጅ በመሸጥ ማስተላለፍ ይፈልጋል


Reporter(Oct 26, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከተውን ንብረት በግልጽ ሐራጅ በመሸጥ ማስተላለፍ ይፈልጋል።

/

የተበዳሪዉ ስም

ቅርንጫፍ

የንብረት አስያዥ ስም

የመያዣ ንብረቱ መለያ

የሐራጅ መነሻ ዋጋ /ብር/

ሐራጁ የሚከናወንበት ቦታ ቀን እና ሰዓት

አድራሻ

የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር

የይዞታው ስፋት

ይዞታው የሚሰጠው አገልግሎት

1

አቶ ሰለሞን አስፋ ተፈራ

መካነ ሰላም ቅርንጫፍ

አቶ ሰለሞን አሰፋ ተፈራ

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ከተማ ቀበሌ 03

1612/2012

150

ይዞታው የተገኘው በምሪት ለመኖሪያ ቤት መስሪያ በሊዝ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ግንባታው ተጠናቆ በመኖሪያነት እያገለገለ የሚገኝ ቪላ ቤት ነው

2,110,910.41

ደሴ ከተማ ሳራ ህንፃ 1 ፎቅ ዲስትሪክት ህግ አገልግሎት ቢሮ ውስጥ በቀን 22/03/2018 . ከጠዋቱ 300-400 ሰዓት

ማሳሰቢያ

1. ማንውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4 በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው።

2. ሐራጁ የሚከናወነዉ ደሴ ከተማ በሚገኘዉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደሴ ዲስትሪክት ህግ አገልግሎት ቢሮ (ደሴ ከተማ ሳራ ህንፃ 1 ፎቅ) ውስጥ ነው።

3. የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ ደንብ እና መተዳደርያ ደንብ ወይም የተመዘገበ እና በጠቅላላ ጉባኤ የተፈረመ ቃለ ጉባኤ የያዘ እና በማህበሩቱ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል።

4. ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በባንኩ የስራ ሰዓት አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ ንብረቱ በሚገኝት አዳራሽ በመገኘት (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መካነ ሰላም ቅርንጫፍ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት) መጎብኘት ይቻላል።

5. የጨረታ አሸናፊ ያሸነፈበት ቀሪ ገንዘብ 15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል:: ሐራጁን ላላሸነፉ ተጫራቾች ሲፒኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል

6. የስም ማዛወሪያ ክፍያ፣ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ እና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮች ገዢው/አሸናፊው/ ይከፍላል።

7. በሐራጁ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪው እና ንብረት አስያዥው ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው።

8. ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ደሴ ከተማ በሚገኘው ደሴ ዲስትሪክት 1 ፎቅ ህግ አገልግሎት ቢሮ በአካል ቀርቦ ወይም በስልክ ቁጥር 033 311 8304 በመደወል ማነጋገር ይቻላል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደሴ ዲስትሪክት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *