Your cart is currently empty!
ዳሽን ባንክ ንብረት የመኖርያ ቤት ባለበት ሁኔታ በሐራጅ ይሸጣል
Reporter(Oct 26, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
የሐራጅ ቁጥር ዳባ/0029/25
ዳሽን ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሠረት የሚከተሉትን ተበዳሪ ወይም አስያዥ ንብረት ባለበት ሁኔታ በሐራጅ ይሸጣል::
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
የአስያዥ ስም |
ለጨረታው የቀረበው ንብረትና የቦታው ስፋት |
የጨረታው መነሻ ዋጋው(ብር) |
የጨረታው የሚካሄድበት |
||||
|
ለጨረታው የቀረበው ንብረት |
ከተማ፣ወረዳ፣ ቀበሌ |
የካርታ ቁጥር |
የቦታ ስፋት |
ቀን |
ሰዓት |
|||||
|
1 |
ናስር ራሺድ መሀሙድ |
ጋራድ ዊልዋል |
ወ/ሮ ዘሀራ ሀዲ ሃሮሽ |
የመኖርያ ቤት |
ጂግጅጋ ከተማ ቀበሌ 16 |
40936/2014 |
400 ካ.ሜ |
2,201,017 |
ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም |
4:00 – 6:00 |
ማሳሰቢያ
1. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(C.P.O) በዳሽን ባንክ አ.ማ. በማሰራት በጨረታው ዕለት ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ::
2. ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት አድራሻ ይካሄዳል::
3. የሐራጁ አሸናፊ /ገዢ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈለው ግብር፣ታክስ ፣ውዝፍ የሊዝ ክፍያ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) እና ሌላ ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ወጪዎችን ገዢው/አሸናፊው/ ይከፍላል::
4. ከፍተኛ ዋጋ የሰጠዉ ተጫራች በጨረታዉ አሸናፊ ነዉ የሚባለዉ ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰዉ ነዉ::
5. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑን ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል:: ባይከፍል ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም:: በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል:: በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያሲያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል::
6. በጨረታው ላይ አስያዥና ተበዳሪ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ፤ ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል::
7. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሠዓት 10 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል::
8. ጨረታው ተጀምሮ በተቀመጠው ሰዓት ውስጥ ካልተጠንቀቀ ሊራዘም ይችላል::
9. ባንኩ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111-704-038 ወይም 0111-704-976 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::
ዳሽን ባንክ አ.ማ.