Your cart is currently empty!
መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃላ/የተ ኤሌክትሮኒክስ፣ ላፕቶፕና ሞባይል ቀፎ እና የሞተር ብስክሌት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 28, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃላ/የተ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
- ሎት 1 – ኤሌክትሮኒክስ (ላፕቶፕና ሞባይል ቀፎ እና
- ሎት 2 – የሞተር ብስክሌት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin No/ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
2. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራንቲ ዋስትና/ ወይም ሲፒኦ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
3. የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነበት የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆነ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዘ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (CPO) ሲያስይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው አንዱ ወይም በጥቅል ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
4. ማንኛውም ተጫራች ሰነዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ አና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታ ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
6. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 350 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ101 ተከታታይ የስራ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 101 መግዛት ይቻላል፡፡
7. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ ተከታታይ የስራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን ተከታታይ ቀናት ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት በ8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
8.ቅዳሜ የዩኒየኑ የስራ ቀን ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
9.የጨረታው ተወዳዳሪዎች ተወካዮቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን የተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
10.የጨረታው አሸናፊ በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10% /አስር በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለባቸው፡፡
11.ከአንድ ሎት ውስጥ ቀንሶ (መርጦ) መሙላት አይቻልም አሸናፊው የሚለየው በተናጠል ይሆናል፡፡አሸናፊው ያሸነፈውን በፍትህ ውል ከተመርመረ (ከተመዘገበ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል/ይሸፍናል፡፡
12.የሚገዛን ንብረት (እቃ) ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ማንኛውንም የወዛደር ማስጫኛ አና የትራንስፖርት ወጪ በአሸናፊው የሚሸፍን ይሆናል፡፡ የሚገዛ እቃ ብዛት አና መለያ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኝ ይገኛል፡፡
13.በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማ የግዢና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
14.የኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15.ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር፡- 09-11-59-05-34/ 09-10-63-46-46 መጠየቅ ይቻላል፡፡
መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃላ/የተ