ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ በድርጅቱ ለታቀፉ ተማሪዎች የሚሆን የመማሪያ ቁሳቁስ ደብተር፣ ቢክ እስክሪብቶ፣ እርሳስ እና ደስታ ወረቀት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 27, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ

ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ መንግሥታዊ ያልሆነ ግብረ ሰናይ ድርጅት ከፕላን ኢንተርናሽናል ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በበጀት ዓመቱ እቅድ መሰረት በድርጅቱ ለታቀፉ ተማሪዎች የሚሆን የመማሪያ ቁሳቁስ ደብተር፣ ቢክ እስክሪብቶ፣ እርሳስ እና ደስታ ወረቀት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

.

የዕቃው አይነት

መለኪያ

ብዛት

ምርመራ/አስተያየት

1

የተለበደ ደብተር (ሲነር ላይን) ባለ 50 ገጽ

በቁጥር

 

79776

 

የተለበደ

 

2

ቢክ እስክሪብቶ ኬንያ አንደኛው

በቁጥር

 

79776

 

ኦርጅናል

 

3

ዶት ፔነሲል

 

በቁጥር

 

79776

 

 

4

ደስታ ወረቀት((ሲነር ላይን)

 

ሪም

 

350

 

አንደኛ ደረጃ/ኦርጅናል

 

በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ቢያንስ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1. በዘርፉ የዘመኑን የታደሰ የንግድና የታደሰ የዋና ምዝገባ ፈቃዳቸውን፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት፣ በጨረታ እንድትሳተፉ ለዘመኑ በጀት ዓመት ብቻ የሚያገለግል የምስክር ወረቀት እና ቲን ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒውን በማያያዝ የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ሰባት የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30- 6፡30 እና ከሰዓት 7፡30 11:30 ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በማያያዝ ዲላ በሚገኘው ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ ጽ/ቤት ሂሳብ ክፍል በመምጣት መግዛት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒውን በስም በታሸገ ኤንቬሎፕ(ፖስታ) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የጨረታውን ጠቅላላ ዋጋ 2% ሁለት በመቶ) ሲፒኦ በሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ ስም ተሰርቶ በኦርጅናል የጨረታ ሰነድ ውስጥ በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከሰባተኛው/7ኛው ቀን በኋላ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ድረስ ለዚህ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዕለቱ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ዲላ ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

4.ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር፡-046 331 0049/046-331-3145 ዘወትር በሥራ ሰዓት ደውሎ መጠየቅና መረዳት ይቻላል።

አድራሻ፡- ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ ዲላ ከተማ ከዲላይት ኢንተርናሽናል ሆቴል 100 ሜትር ገባ ብሎ።
ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *