በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የ102ኛ ኮማንዶ ክ/ጦር የተለያዩ የፅህፈት ዕቃዎች፣ የተለያዩ የፅዳት እና የማገገሚያ ዕቃዎች እና የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 28, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡-የል/ዘ/ዕዝ/መ/መ102ኛ
ኮ/ክ/ጦር01/2018

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የ102ኛ ኮማንዶ ክ/ጦር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1 – የተለያዩ የፅህፈት ዕቃዎች፣
  • ሎት 2 – የተለያዩ የፅዳት እና የማገገሚያ ዕቃዎች፣
  • ሎት 3 – የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎች

 ስለዚህ በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች፡፡

1. ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ዘርፍ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ያላቸው እና የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡

2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው ብር መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

3. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ለአንድ ሎት በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀን ውስጥ ባሉት የስራ ቀናት አዲስ አበባ አምባሳደር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የግዢ ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ከጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ግዢ ክፍል ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. ጨረታው ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ በሚገኝ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡

6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-09-13-75-24-98 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የ102ኛ ኮማንዶ ክ/ጦር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *