Your cart is currently empty!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በስሩ ላሉ መስሪያ ቤቶች የሚውል ሞተር ሳይክሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 28, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በስሩ ላሉ መስሪያ ቤቶች የሚውል ሞተር ሳይክሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለ እቃዎቹ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 150 (አንድ መቶ ሃምሳ) ብር ብቻ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በምስ/አዘ/በር/ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በመምጣት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ፡፡
በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፤
2. የቫት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
3. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስረከቢያ /CPO/ 20,000 ብር ማቅረብ የሚችሉ፤
5. ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉትን እቃ ምስ/አዘ/በ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ የትራንስፖርት የማስጫኛና የማውረጃ ሳይጨምር በጨረታው ሰነድ ላይ በመሙላት ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. አንዱ ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
8. ጨረታው በ15ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል፡፡
9. በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ ፋይናንሺያል ዋጋዎች በግልጽና በጥራት የሚታዩና ስርዝ ወይም ድልዝ ያልሆነ መሆን አለባቸው፡፡
10. ተጫራቾች በሚፈልጉት ዕቃ ላይ መወዳደር ይችላሉ፤ ሆኖም ለአንድ እቃ ከተጠየቀው ብዛት አሳንሶ ማቅረብ አይቻልም፡፡
11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. ወረዳው ከአዲስ አበባ ርቀቱ 221 ኪሎ ሜትር ሲሆን 176 ኪሎ ሜትር አስፓልት እና 45 ኪሎ ሜትር ፒስታ መንገድ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-09-27-17-59-14/ 09-33-62-02-20
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት