Your cart is currently empty!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሰጡ 150 CC ቦክሰር ሞተር ሳይክል ለባለአራት ማርሽና ለባለአምስት ማርሽ ሞተር መለዋወጫ እቃዎች (spare part) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 27, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መስያ ቁጥር G/G/W/W-0004/2018 ዓ.ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሰጡ 150 CC ቦክሰር ሞተር ሳይክል ለባለአራት ማርሽና ለባለአምስት ማርሽ ሞተር መለዋወጫ እቃዎች (spare part) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም:-
1. የ2018 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ፣ የቫትና የቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. በአቅራቢነት የምስክር ወረቀት በኦላይን /online/ ሲስተም የተመዘገነቡ መሆን አለባቸው።
3. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱ ጠቅለው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆነ ከድርጅቱ ሕጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው።
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 100 ብር/አንድ መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመቅረብ የጨረታው ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
5. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ብር 10,000(አስር ሺህ ብር) በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው።
6. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት ሲያቀርቡ፡– ሀ/ ቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት እና ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒውን ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በማሸግ ከላይ የተጠቀሱት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ከገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. የጨረታው ማስከበሪያ ሲፒኦ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማሰራት አለበት።
8. የጨረታው ሰነድ በ15ኛው ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል። በዚያውኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ደግሞ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
9. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ ፡–
1. በግዢ ኤጀንሲ በዕቃ አቅርቦት ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶችም መወዳደር አይችሉም።
2. ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉት እቃዎች የጥራት ችግር ያለባቸው መሆናቸው በቴክኒክ ጥራት ኮሚቴ ከተረጋገጠ ተመላሽ መሆኑን፣
3. ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉት ማንኛውም እቃ የወረዳው ማዕከል ማለትም ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የወረዳው ማዕከል ርቀት ከአዲስ አበባ 116 ኪሜ ነው።
በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት