Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኤቨንት ኦርጋናይዘር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 28, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ /በድጋሚ የወጣ/
የጨረታ ቁጥር፡– ስ.ክ.ብ.ው.ጨ 003/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኤቨንት ኦርጋናይዘር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡–
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ሆነው ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉና መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ብር 75,000 /ሰባ አምስት ሺህ ብር/ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል 5 ኪሎ ከሚገኘው ስፖርት ኮሚሽን ህንፃ 6ኛ ፎቅ ግዢና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ዋናውን እና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም ግን የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
- ዘግይቶ የመጣ የጨረታ ፖስታ ተቀባይነት የለውም።
- ቢሮው ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– አምስት ኪሎ ብሔራዊ ሙዚየም ጀርባ የስፖርት ኮሚሽን ህንፃ 6ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011-140-7110
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ