ቦሌ ማተሚያ ኃላ/የተ/የግ ማህበር የተለያዩ የሰራተኛ የደንብ ልብሶች፣ ጫማዎች፣ ሸሚዞች፣ ከረቫት፣ ኮፊያና የዝናብ ልብስ፣ ልዩ ልዩ ኬሚካሎች፣ ቀለሞችና ፕሌት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 28, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የሀገር ውስጥ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

ቦሌ ማተሚያ ኃላ/የተ/የግ ማህበር

  • ሎት 1. የተለያዩ የሰራተኛ የደንብ ልብሶች፣ ጫማዎች፣ ሸሚዞች፣ ከረቫት፣ ኮፊያና የዝናብ ልብስ፣
  • ሎት 2 ልዩ ልዩ ኬሚካሎች፣ ቀለሞችና ፕሌት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፤ የንግድ ሰርተፊኬት እና ሌሎችም የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ቢሮ ቁጥር 10 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ድረስ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሯችን መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የዋጋቸውን 2%፣ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶችን በአንድ ፖስታ አሽገው የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከግዥ ክፍል በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ፡፡

5. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አይነት ለጥራት ሙከራ ይሆን ዘንድ ናሙና/ ሳምፕል ከሰነዶቻቸው ጋር አብሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

6. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ተእታ 15% በማካተት በግልጽ ጽፈው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ለሙሉ ልብስ፣ ቱታ፣ ገዋንና ሸሚዝ የሚሳተፉ ተጫራቾች ስለዝርዝር አፈጻጸሙ ቅድሚያ ውል በመፈረም ከማተሚያ ማህበሩ ዘንድ በአካል በመምጣት የእያንዳንዱን ሰራተኛ ልኬት በመውሰድና ጨርቅ በራሳቸው አቅርበው በልኬቱ መሰረት በትክክል ሰፍተው ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

8. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት በማህበሩ የስብሰባ አዳራሽ/ የግዢ ክፍል ይከፈታል፡፡

9. ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡-011-15 15 50 05/ 011-5-51-88-72 ፋክስ ቁጥር፡-011-5-51-86-96
ፖ.ሳ.ቁጥር፡-2365

ቦሌ ማተሚያ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *