Your cart is currently empty!
ኢትዮጵያን እናክማት ሰብዓዊና በጎ አድራጎት ድርጅት የሁለት ዓመት (እ.ኤ.አ 2016 -2017) የሂሳብ እንቅስቃሴ በታወቁ የውጭ ኦዲተሮች ሂሳቡን ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 28, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የኦዲተር ጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮጵያን እናክማት ሰብዓዊና በጎ አድራጎት ድርጅት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በጎ አድራጎት ድርጅት ሆኖ ጥቅምት 16 ቀን 2015 ዓ.ም በፈቃድ ቁጥር 6483 ተመዝግቦ በሥራ ላይ ያለ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡
በዚሁ መሠረት የድርጅቱን የሁለት ዓመት (እ.ኤ.አ 2016 -2017 ) የሂሳብ እንቅስቃሴ በታወቁ የውጭ ኦዲተሮች ሂሳቡን ኦዲት ማስደረግ ስለሚፈልግ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ ወቅታዊ እና አስፈላጊ መረጃቸው የተሟላ የኦዲት ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ አሥር ቀናት ውስጥ በደጃች ውቤ ሰፈር በሚገኘው ኢትኤል ሕንጸ 4ኛ ፎቅ ቁጥር 401 በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ የሥራ ዝርዝራቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ኢትዮጵያን እናክማት ሰብዓዊና በጎ አድራጎት ድርጅት