የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በሚ/አ/ከ/አስ/ር ስር ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገ/ት የሚውሉ ጽ/መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 28, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በሚ/አ/ከ/አስ/ር ስር ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገ/ት የሚውሉ

  • ሎት 1 – ጽ/መሳሪያ፣
  • ሎት 2 – ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
  3. በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
  5. ግብር ስለመክፈላቸው ከገቢዎች መ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  6. የጨረታ ሰነድ ከግዥ ኬዝ ቲም የሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን /በነጻ/ በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
  7. የጨረታ ሰነዱ ሞልተው ሲመልሱ ህጋዊነት ሰነድ እና ፋይናንሻል የተሞላበትን ሰነድ 1 ኦሪጅናልና 1 ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ቼክ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ለሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በማለት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
  10. ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው።
  11. በጨረታ ማስታወቂያ ላይ የቃላት ወይም የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጠው የበለጠ ተቀባይነት ይኖረዋል።
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *