Your cart is currently empty!
ሐበሻ ቢራ አክሲዮን ማህበር በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ በማወዳደር ከአሸናፊው ድርጅቶች ጋር ለምርት ግብአት የሚሆን ነጭ የተጣራ ስኳር ለማቅረብ ተፈራርሞ መስራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 29, 2025)
Reporter(Oct 29, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ነጭ የተጣራ ስኳር ግዢ የጨረታ ማሳወቂያ
ሐበሻ ቢራ አክሲዮን ማህበር በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ በማወዳደር ከአሸናፊው ድርጅቶች ጋር ለምርት ግብአት የሚሆን ነጭ የተጣራ ስኳር ለማቅረብ ተፈራርሞ መስራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች፡–
- ጥራቱን እና ደረጃውን የጠበቀ፣ ለምግብ እና መጠጥ ምርት ተስማሚ የሆነ ነጭ የተጣራ ስኳር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ስኳሩ ከብክለት የጸዳ መሆኑን፣ ሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ የጥራት ማረጋገጫዎችን የተከተለ እና እርጥበትን መቋቋም በሚችል ማሸጊያዎች መታሸጉን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል።
- 4 ሚሊዮን ኪሎ (4,000 ቶን) ስኳር ማቅረብ መቻል ይኖርባቸዋል።
- በስራ ላይ ምንም አይነት መስተጓጎል አለመኖሩን ለማረጋገጥ በቅድመ–ስምምነት መሰረት ስኳሩን ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
- ንጽህና፣ የእርጥበት መጠን እና ጎጂ ንጥረ ነገሮች አለመኖር ያሉ የጥራት መለኪያዎችን ለማረጋገጥ ለእያንዳንዱ ባች የትንታኔ ሰርተፍኬት (certificate of Analysis) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጉድለት ያለባቸውን አቅርቦቶችን ያለምንም ተጨማሪ ወጪ መተካት ይኖርባቸዋል።
- በዘርፉ የተሰማሩ መሆናቸውን የሚገልፅ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት፣ የምዝገባ ፈቃድ ሰርተፍኬት ሊኖራቸው ይገባል።
- ተጫራቾች ወደዋና መስሪያ ቤት በመምጣት እስከ ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም 7፡00 ሰዓት (ሰባት ሰዓት) ድረስ የማይመለስ 500 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ መቀበል ይኖርባቸዋል። ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት (ስምንት ሰዓት) ድረስ ተጫራቾች በአካል ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ወይም በኢሜል አድራሻ factoryprocurement@habeshabreweries.com በመጠቀም ጨረታውን መሳተፍ ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ድርጅቱ ምላሾቹ ከተቀበለ በኋላ የጨረታ ሰነዶችን በመገምገም የተመረጡትን ያሸነፉትን አቅራቢዎችን ያሳወቃል።
አድራሻ፡- ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አክሲዮን ማህበር ቦሌ ካርጎ ፊት ለፊት
ስ.ቁ 0965683654/0911478704
አዲስ አበባ፣
ኢትዮጵያ
ሐበሻ ቢራ አክሲዮን ማህበር