Your cart is currently empty!
በልደታ ከፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች ለሚያሠራቸው የግንባታ ሥራዎች በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 29, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂ
የጨረታ ቁጥር L/S/C/D/C/W/0-001/2018.
በልደታ ከፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች ለሚያሠራቸው የግንባታ ሥራዎች በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የተሟላ የሰው ኃይል እና ማሽነሪዎች በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ሥራውን ማጠናቀቅ የሚችል እና የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በሟሟላት የጨረታ ሰነዱን በአካል በመምጣት ብቻ መውሰድ ይችላሉ።
|
ሎት |
የሥራው ዓይነት |
የግንባታ ጊዜ (በቀን) |
የጨረታ አየር ላይ የሚቆይበት ቀን |
ደረጃ
|
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን |
የጨረታ ሰነድ የሚገባበት ቀን |
የጨረታ መክፈቻ ቀን
|
|
01 |
የሕፃናት ማቆያ ግንባታ ሥራ |
45 ቀናት |
ይህ ማስታወቂያ ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት |
BC7 እና ከዚያ በላይ
|
200,000 ብር ትእዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና |
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 22ኛ ቀን ጠዋት ከ3፡00 እስከ 4፡00 ሰዓት |
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 22ኛ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት |
- ለሥራው ሕጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የ2018 ዓ.ም.የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ወይም የ2017 ዓም ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው ግዴታቸውን እየተወጣ መሆናቸውን የሚገልጽ እና በዓም በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል የሚያቀርቡ ሆነው ጨረታውን አሸናፊ ከሆኑ ግን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ውል ከማሠራቸው በፊት ማቅረብ የሚችሉ ፣ የ2018 ፈቃድ የደሱም ቢሆኑም ሁሉም ተጫራቾች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከፌደራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው /ከሁለቱም/ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (supplier list)፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆነና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡ በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ሥራ ላላቸው ሥራ ተቋራጮች ደግሞ ያላቸው የግንባታ አፈፃፀም ከ75% በላይ መሆኑን የሚገልፅና መልካም አፈፃፀም (Good Performance) ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ ሁሉም ተወዳዳሪ ተቋራጮች ቀድሞ ለሠሩት ፕሮጀክት ከሠሩበት ተቋም የቅርብ ጊዜ የመልካም የሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰአት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሕንፃ ዲዛይን እና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 503 ከምህንድስና ግዢ ቡድን ክፍል ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናው (Original)፤ የማይመለስ ቅጂ(CPO)፤ ፍላሽ እና ማህተም ይዞ በመቅረብ የማይመለስ ብር 1,000 ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ በጨረታው የቴክኒካል ሰነድ ከክፍል አንድ እስከ ሦስት ባለው መሰረት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በልደታ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀዉ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID_BOND_ or BID SECURITY) በባንክ ትእዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና / UNCONDITIONAL BANK GUARANTEE/ ከላይ በተጠቀሰው የብር መጠን በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት (Lideta Sub City Design and Construction Works Office ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድን በጨረታው ሰነድ በተቀመጠው መመሪያ መሰረት የመጫረቻ ሰነድ ማዘጋጀት አለባቸው፡
- ውድድሩ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦርጂናል እና ቴክኒካል ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሺያል አንድ ኦርጂናል እና ፋይናንሽያል ሁለት ኮፒ በማሸግ በድምሩ ስድስት ሰነድ ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሦስትናም (BID BOND or BID SECURITY) ሰብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ ላይ ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ በተጨማሪም በሰም የታሸገውን 6 ፖስታ የፋይናንሻል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በሰም በማሸግ እና ቴክኒካል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በሰም በማሸግ ሁለቱን ፖስታና የሮው ፖስታውን በአንድ እናት ፖስታ በሰም በማሸግ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የሥራ አይነት ስም በመጻፍ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዶችን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት (ሙሉ በሙሉ ባይገኙ የሚከፈት ይሆናል)፡፡
- ተጫራቾች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ በግንባታ እና በዲዛይን በንኡስ ተቋራጭነት ለማሳተፍ የወጣውን መመሪያ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡ ለዚህም የሚያሳትፉበትን የሥራ ዝርዝሮች በመጥቀስ ከስምምነት ደብዳቤ ጋር አያይዞ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሠሪው መ/ቤት አሸናፊው ካሸነፈበት አጠቃላይ ሥራ 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾች መመሪያን እንዲያነቡ እና የግንባታ ሳይቱን ማየት ይመከራል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ባለሙያዎች በድርጅታቸው ውስጥ ብቻ የሚሠሩ ወይም ለድርጅቱ ብቻ የፈረሙ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ በድርጅቱ ኃላፊ ወይም ተመሳሳይ ተግባር እና ሥልጣን በተሰጠው አካል እና በተቀጣሪው (በፈራሚው) ባለሙያ የተፈረመ ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ አንድ ባለሙያ ከአንድ ሥራ ተቋራጭ በላይ ፈርሞ ከተገኘ ያስፈረሙት ሥራ ተቋራጮች ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናል፡፡
- የትኛውንም ከላይ የተዘረዘሩትን ሆነ በጨረታው ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ሕጎች አለማክበር፣ በሚያስገቡት የመጫረቻ ሰነዶች በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ፣ በዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (Unsigned Rate Correction) እና በዋጋ ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Rate Correction) ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡ በተጨማሪም በሥራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የሥራ አይተም ላይ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ሥራውን በነጻ እንደሚሠራ ይወሰዳል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የድርጅቱ የሥራ ልምድ እና ማንኛውም በቴክኒካል የተጠየቁ ዶክመንቶችን አሠሪ መሥሪያ ቤት ኦሪጅናል ዶከመንት የመጠየቅ እና ዶከመንቶቹን ከሰጠው አካል የማጣራት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ምሕንድስና ግዢ ቡድን ካፍዕ በአካል በመቅረብ መረዳት ይቻላል።
- አድራሻ፡- ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ወደ አገነት የሚወስደው መንገድ ተሰፋ ኮከብ ት/ቤት አጠገብ የሚገኘው የክፍለ ከተማው ሕንፃ ልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽቤት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 503 ከምህንድስና ግዢ ቡድን ከፍል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት