Your cart is currently empty!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የቤተ ክርስቲያኗ ንብረት የሆነውን ለንግድ የሚሆን ቤትን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል
Reporter(Oct 29, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የንግድ ቤት ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
1. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የቤተ ክርስቲያኗ ንብረት የሆነውን ለንግድ የሚሆን ቤትን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
2. የቤቱ አድራሻ፡- በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የሚገኙ ሁለት መጋዘኖች፣ በቸርቸር ጐዳን ትንሣኤ ሕንጻ የሚገኝ ንግድ ቤት፣ ፒያሳ መብራት ኃይል አጠገብ የዘውዲቱ ሕንጻ ቴራዝ፣
3. በተራ ቁጥር 9 ላይ ያለ የንብረት ጨረታ፣
4. መንግሥታዊ ድርጅት ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ተወዳዳሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ ሆኖ ከሚገለገልበት ደብር የድጋፍ ደብዳቤና የአባልነት መታወቂያ ማቅረብ የሚችል፣
5. ተጫራች በጨረታው አሸናፊ ሆኖ ቤቱን ከተረከበ በኋላ የውሃና የመብራት ፍጆታ ራሱ ይከፍላል።
6. ድርጅቱ ለኪራይ ያቀረባቸውን መጋዘን፣ንግድ ቤትና ቴራዝ በጨረታ ተወዳድሮ ለመከራየት የሚፍልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡00 ክፍሉን በአካል ቀርቦ በማየት ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ከፍሎ ገዝቶ በመሙላት በታሸገ ኢንቫሎፕ በድርጅቱ ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለበት።
7. ተጫራቾች ነጋዴ ከሆኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ደረሰኝ፣ ኢንቨስተር ከሆነ የኢንቨስትመንት ፈቃድ፣ የንግድ ማኅበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሑፍ፣ የሙያ አገልግሎት ሰጪ ከሆነ የሙያ ፈቃዱን ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
8. ተጫራቾች በጥቅልም ሆነ በተናጥል ሲወዳደሩ የሚጫረቱበት ክፍል የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 5000.00 በማስያዝ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዳቸው በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከሚያቀርቡ የጨረታ ሰነድ ዋጋ ጋር ዋናውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
1. ቤቱን ከፋፍሎ ለሦስተኛ ወገን ማስተላለፍ አይቻልም።
9. በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ፒያሳ የሚገኘው ኤሌትሪክ ሕንጻ አጠገብ ዘውዲቱ ሕንጻ በሚባለው ግቢ ውስጥ የሚገኙ ንቃይ ቆርቆሮዎችና የተለያዩ ንብረቶች፣
10. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ተዘግቶ በማግስቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት በድርጅቱ ጽ/ቤት ይከፈታል።
11. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. የጨረታ መነሻ ዋጋ እና ዝርዝር መመሪያ ከጨረታው ሰነድ ላይ ማግኘት ይቻላል።
ለበለጠ መረጃ
በስ.ቁ. 011 156-6378
በድርጅቱ ጽ/ቤት በአካል ቀርበው ይጠይቁ፡