በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ወለጋ ዞን በጎቡ ሰዮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለጎቡ ሰዮ ወረዳ መንገድ እና ሎጅስቲክ ጽ/ቤት የተለያዩ ማሽኖችን መከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 29, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ወለጋ ዞን በጎቡ ሰዮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለጎቡ ሰዮ ወረዳ መንገድ እና ሎጅስቲክ ጽ/ቤት የተለያዩ ማሽኖችን መከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ግሬደር፣ እስካቫተር፤ ሩሎ፤ ስኖ ትራክ እና ሻወር ትራክ ፍቃድ ያላቸውን ማሽን ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በወረዳው የካፒታል በጀት እና በማህበረስብ ተሳትፎ ፈንድ አወዳድሮ ለማስጠገን ማከራየት ይፈልጋል፡፡

ዚህ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፤

  1.  የማሸኖች ኪራይ ንግድ ፍቃድ የ2018 ያለው፡፡
  2.  የቲን ቁጥር ያለው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
  3. 2017 እና 2018 ግብር የከፈለ መሆኑን ከገቢዎች ቢሮ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. ተወዳዳሪዎች ማሽኖቹ የተመረቱበት ሀገር የሞዴሎቹ ቁጥር የተመረተበትን አመት በግልጽ ጽፎ ማቅረብ የሚችል፡፡
  5.  በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ፡፡
  6.  ለመንገድ ስራ ጥገና እና ለማሽን ኪራይ ተፈላጊዎች፡፡
    1. ግሬደር ሞዴሉ 140H/K/G የሆነ የፈረስ ጉልበቱ 185 በላይ ሆኖ የምርት ዘመኑ 2012 G.C የሆነ፡፡
    2. እስካቫተር ሞዴሉ CL/DL 325 እና ከእሱ በላይ ሆኖ የፈረስ ጉልበቱ 318 በላይ የምርት ዘመኑ 2012 G.C የሆነ፡፡
    3. ሲኖትራክ ሞዴሉ 325 በላይ የሆነ እና የፈረስ ጉልበቱ 336 እና ከዚያ በላይ ሆኖ የምርት ዘመን 2020 G.C ሆኖ ዋጋው እስፔሲፊኬሽኑ የሚከፈል ሆኖ ተወዳዳሪው ዋጋውን የሚሞላ ይሆናል።
    4. ሩሎ ሞዴሉ BW4AD እና ከዚያ በላይ የፈረስ ጉልበቱ 160 እና ከዚያ በላይ፡፡
    5. ሻውር ትራክ ሞዴሉ 325 በላይ እና የፈረስ ጉልበቱ 336 እና ከዚያ በላይ የምርት ዘመኑ 2016 G.C የሆነ እና ከዚያ በላይ፡፡
  7. የባለንብረት ሊብሬ ሰነድ ማቅረብ እና ማሽኑ ጉዳት ከደረሰበት በራሱ ወጪ አሰርቶ በአጭር ጊዜ በ10 ቀን ውስጥ ማሰራት ወይም ተመሳሳይ ማሽን መተካት የሚችል፡፡
  8.  የአከራዩ አድራሻ በሰነድ የተረጋገጠ እና ወረዳውን ቀበሌውን የቤት ቁጥር እና የስልክ ቁጥር ያለው፡፡
  9. ማንኛውም ተወዳዳሪ ለዚህ የሚያስፈልግ የምስክር ወረቀት ከ2015 ወዲህ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. ማንኛውም ተወዳዳሪ ምግብ እና መጠጥ ማደሪያ ቦታ እና የማሽኖቹ ጥበቃ ሰራተኛ እንደዚሁም ለሰርቪስ የሚያስፈልግ መኪና/ቢ ካፕ/በራሱ አቅርቦ በስራው ቦታ መገኘት እና ነዳጅ መሙላት እና ሌሎች ወጪዎችን በራሱ የሚያሟላ መሆን አለበት፡፡
  11. የማሽኖች መጫኛ እና ማውረጃ የደርሶ መልስ ዋጋው በተወዳዳሪው የሚሸፈን መሆኑ፡፡
  12. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ የሚያሲዝ ሆኖ የጨረታ ማስከበሪያው ተወዳዳሪዎች አሸናፊው ከተለየ ከ5/አምስት/ ቀን በኋላ የሚመለስ ሆኖ ግን የመስሪያ ቤቱን ውስጥ ደንብ የማያከብር ከሆነ የጨረታ ሰነዱ ማስከበሪያ ካለምንም ጥያቄ ከተወዳዳሪው የሚወረስ ይሆናል፡፡ እንደዚሁም አሸናፊው ማሸነፉን ታውቆ በውሉ መሰረት ማሸኖቹን ማቅረብ ካቃተው የጨረታ ማስከበሪያ እና የውሉን ማስከበሪያ የሚወረስ ይሆናል፡፡
  13.  የውልማስከበሪያ ብር አጠቃላይ ከተሰጠው የስራ ውል ውስጥ 10%ቱን የሚያሲዝ ሁኖ የውሉ ማስከበሪያ ስራ መጠናቀቁ ከተረጋገጠ በኋላ ርክክብ ተደርጎ የሚመለስ ይሆናል፡፡
  14. ተወዳዳሪው የጨረታውን የማሸኖችን ኪራይ ያሸነፈ በአካል ቀርቦ ውሉን መፈረም አለበት፡፡
  15. ተወዳዳሪው ለስራ የሚያስፈልገውን የጨረታ ሰነድ ብር 1,500 /አንድ ሺህ አምስት መቶ/ ብቻ በመከፈል በጎቡ ሰዮ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ ከፍሎ የጨረታ ሰነዱን ወስዶ ጨረታውን ለጎቡ ሰዮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ያስገባል፡፡
  16.  የመንገድ ጥገና ስራውን ጥራት እንዲኖረው የጎቡ ሰዮ ወረዳ መንገድና ሎጂስቲክ ጽ/ቤት እና የጎቡ ሰዮ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት በጋራ በመሆን የስራውን ጥራት መቆጣጠር እና ጥራት ከሌለው ለማስቆም መብት አላቸው፡፡
  17.  ተወዳዳሪው የጨረታ ሰነዱን በአራት/4/ ፖስታ አሽጎ ማቅረብ አለበት፡፡
    1. የቴክኒክ ፖስታው ኦርጂናል እና ኮፒው ብቻ ለብቻ በካኪ ፖስታ በሰም ኤንቨሎፕ ታሽጎ ማህተም ተደርጎ ብቻ ለብቻ ፖስታ ላይ ተፈርሞ መቅረብ አለበት፡፡
    2. የፋይናንስ ፖስታ ኦርጂናል እና ኮፒው ብቻ ለብቻ በካኪ ፖስታ በሰም ኤንቨሎፕ ታሽጎ ማህተም ተደርጎ ብቻ ለብቻ ፖስታ ላይ ተፈርሞ መቅረብ አለበት፡፡
    3. ሁሉም የቴክኒክ እና የፋይናንስ ፖስታ ደግሞ በትልቁ ፖስታ በአንድ ላይ በሰም ኤንቬሎፕ ታሽጎ ተፈርሞበት ማህተም ተደርጎ በማስመዝገብ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
  18.  ጨረታው ለ21 ቀን ሀያ አንድ/ በስራ ሰዓት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ ከ9/2/2018 እስከ 17/3/2018 4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ተዘግቶ በዚሁ ቀን 17/3/2018 በ4፡30 ሰዓት ተወዳዳሪው /ህጋዊ ተወካይ/ ባለበት በጎቡ ሰዮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በኃላፊው ክፍል የሚከፈት ሆኖ የጨረታ ሰነድ ያስገባው ተወዳዳሪ ቢቀር ባይገኝ⁄ ለመክፈት የሚከለክል እንዳልሆነ እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዋጋ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ሁሉም ፖስታ አድራሻ የስልክ ቁጥር ሊኖረው ይገባል፡
  • ለተጨማሪ መረጃ 0920421365/0917071659 ወይም 0917844339 ስልክ ላይ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

በምስራቅ ወለጋ ዞን  ጎቡ ሰዮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *