Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ የዕቃዎች ግዥ በሀገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 29, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ የዕቃዎች ግዥ በሀገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡–
- በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ጉርድ ሾላ በሚገኘው በፌዴሬሽኑ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት 4፡30 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ዕቃ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የሚጫረቱት በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው።
አድራሻ፡– ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6
ለበለጠ መረጃ፡– 011 647-9794/ 011 647-9578 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ፋክስ 011 645-0879 ፖ.ሳ.ቁ 13336
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን