የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ ጠቅላላ ሥራ እና ሕንፃ ሥራ ተቋራጭ (GC/BC 3) የሆኑ የሀገር ውስጥ ጨረታ ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የአቪዬሽን ፖሊስ G+1 ሕንፃ ግንባታ እና ነባር ፋሲሊቲ ጥገና ፕሮጀክት በዲዛይን እና ግንባታ የውል ዓይነት በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 29, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ -SSNT-T580

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ ጠቅላላ ሥራ እና ሕንፃ ሥራ ተቋራጭ (GC/BC 3) የሆኑ የሀገር ውስጥ ጨረታ ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የአቪዬሽን ፖሊስ G+1 ሕንፃ ግንባታ እና ነባር ፋሲሊቲ ጥገና ፕሮጀክት በዲዛይን እና ግንባታ የውል ዓይነት በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ለሥራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች፣ የዘመኑን የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግሥት ጨረታዎች ለመሳተፍ የሚያገለግል ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E- 99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T580 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy)፣ የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ለ150 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቋም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል። የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ ሥራው ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ በ180 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ይሆናል። ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ኅዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ5:30 ሰዓት ይከፈታል።

ተጨማሪ ማብራሪያ:-
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ ዓስም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ስልክ ቁጥር 011-517-8025
ኢ-ሜይል: Eskedarya@ethiopianairlines.com 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።