ፀደይ ባንክ አ.ማ. ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter(Oct 29, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የመጀመሪያ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

ፀደይ ባንክ አ.ማ. ለአቶ እንዳልካቸው ደመላሽ ነጋ ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዛቸውንና ዝርዝር ሁኔታቸው ከዚህ በታች የተገለጹትን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተቁ

የተበዳሪ ስም

የአስያዥ ስም

የንብረቱ መገኛ እና ካርታ ቁጥር

መነሻ ግምት

1

እንዳልካቸው ደመላሽ

ዓለማየሁ ጎነጠ

 

በአብክመ ጎንደር ከተማ አዘዞ ጠዳ /ከተማ ቀበሌ 20 ካርታ ቁጥር ኢፖልኮ/ ጎን/113/14 ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውል የድርጅት ቤት

37,413,186.11

 

2

እንዳልካቸው ደመላሽ

ስዩም አብርሃ

 

አዲስ አበባ ከተማ የካ /ከተማ ወረዳ 12 ካርታ ቁጥር AA00005120869 B1+G+G2 ዋና እና B1+G ሰርቪስ የያዘ መኖሪያ ቤት

19,763,287.53

 

በመሆኑም ማንኛቸውም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ደንቦችና ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች በጫራታው እንዲሳተፉ እንጋብዛለን።

1. ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ) በፀደይ ባንክ አማ ስም በማሰራት ለጨረታ መስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል

2. በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የድርጅቱን መመስረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ ፤ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበትን የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ሕጋዊ ውክልና ማቅረብ ይኖርበታል።

3. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል

4. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ በጨረታ ያሸነፈውን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። አሸናፊው በ15 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ያሆናል።

5. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ይመለስላቸዋል

6. የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፤ ቫት የሚከፈል ከሆነም እንዲሁ ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማንኛውንም ወጭዎች ይሸፍናል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረው የሊዝ ክፍያ ገዡ ከሚመለከተው የመንግስት አካል አካል ጋር ይዋዋላ።

7. ተጫራቾች ቤቶቹን ሕዳር 12 ቀን 2018 ዓ.ም በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ

8. ጨረታው ሕዳር 20/2018 ዓ.ም በሰንጠረዡ ተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለጸውን በጎንደር ከተማ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የፀደይ ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት ሕንጻ ላይ እንዲሁም በተራ ቁጥ 2 ላይ የተገለጸውን አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ ሜክሲኮ ሰንጋ ተራ ከሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋናው መ/ቤት 9ኛ ፎቅ ላይ ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ይደረጋል

9. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 18 30 31 44


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *