የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለመ/ቤቱ የቢሮ አገልግሎት የሚሰጥ የቢሮ ጥገና ግንባታ ማሰራት ይፈልጋል


Be’kur(Oct 27, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለመ/ቤቱ የቢሮ አገልግሎት የሚሰጥ የቢሮ ጥገና ግንባታ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።

  1. ተጫራቾች ደረጃ 7 እና በላይ በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ያላቸዉ።
  3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና መረጃዉን አብረዉ አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ማዕከላዊ ጎንደር ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  5. ጨረታዉ ከጥቅምት 17/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 7/2018 ዓ.ም በጋዜጣ ወጥቶ ህዳር 8/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በታሸገበት ቀን ልክ ከቀኑ 8፡15 ላይ በማዕከለዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግ/ፋ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በቀኑና በሰዓቱ ቢገኙም ባይገኙም ጨረታዉን ከመክፈት አያግድም። የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ ቀን በተገለፀዉ ሰዓት የሚዘጋና የሚከፈት ይሆናል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከመ/ቤታችን ግዥ /ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ከገንዘብ ያዥ በመሂ/1 ለማስያዛቸዉ የገቢ ደረሰኝ አስቆርጠዉ ከሚወዳደሩበት ሰነድ ጋር አብሮ ፎቶ ኮፒዉን በማሸግ አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸዉንና የቴከኒክ መስፈርቶችን መግለጫና ጠቅላላ ለግንባታዉ ዋጋ ማቅረቢያ አንድ ወጥ በሆነ ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነድ በጥንቃቄ የታሸገ ፖስታ ከላይ በተገለፀው መሰረት እስከ ህዳር 8/2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ ዘወትር በሥራ ስዓት በተዘጋጀዉ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
  8. የስራዉን ዝርዘር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ሙሉ መረጃዉን ማግኘት ይችላሉ።
  9. ወቅታዊ የሥራ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. ማንኛዉም ተጫራች የሚያቀርበዉ የማወዳደሪያ ሀሳብ ማንኛዉንም ታክስና ቫትን፣ የሰዉ ኃይልና ማቴያሉን ሙሉ ወጭ ያካተተ መሆን አለበት።
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
  12. ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ካስፈለገዎት ማዕከለዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 111 44 40 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *