Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በምስራቅ ሸዋ ዞን በአዳሚ ቱሉ ጂዶ ኮምቦልቻ ወረዳ ከአዲስ አበባ 183 ኪሜ እርቀት ላይ ለሚገኘው ለአሉቶ ጂኦተርማል ፕሮጀክት የሚያገለግሉ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ኪራይ አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 30, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/01/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በምስራቅ ሸዋ ዞን በአዳሚ ቱሉ ጂዶ ኮምቦልቻ ወረዳ ከአዲስ አበባ 183 ኪሜ እርቀት ላይ ለሚገኘው ለአሉቶ ጂኦተርማል ፕሮጀክት የሚያገለግሉ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ኪራይ አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግሥት የአቅራቢዎች የአገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት መሣሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሰው ኃይልና ፋይናንስ አስተዳደር ህንጻ ኛ ፎቅ ካሼር ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከግዥ እና ሎጅስቲክስ ህንጻ ምድር ቤት ከጀነሬሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን የኮንክሪት መዳረሻ የመንገድ ሥራ ግዥ በሚመለከት የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ፖስታ የጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/01/2018 የሚል ምልክት በማድረግ 1(አንድ) ኦሪጅናል እና 2(ሁለት) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) ለ60(ስልሳ) ቀን የአገልግሎት ጊዜ የሚቆይ የባንክ ክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power) ስም ተዘጋጅቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ህዳር 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ምድር ቤት ጀነሬሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 011-5 57 95 42 መደወል ይችላሉ ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል