Your cart is currently empty!
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በቡኖ በደሌ ዞን የሚገኝ የዲዴሣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኘው ወረዳው መንገድና ሎጂስቲክ ጽ/ቤት በተለያዩ ቀበሌዎች የሚገኙትን መንገዶች ሕጋዊ የሆኑትን ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማሽነሪ በመከራየት ጠጠር መንገድ ጥገና ማሠራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 31, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በቡኖ በደሌ ዞን የሚገኝ የዲዴሣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኘው ወረዳው መንገድና ሎጂስቲክ ጽ/ቤት በተለያዩ ቀበሌዎች የሚገኙትን መንገዶች ሕጋዊ የሆኑትን ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግሬደር ( caterpillar 140-H) ፣ ዳምፕትራከ፣ እስካቫተር Dosan; ከ340 ፈረስ ጉልበት በላይ የሆነ፣ እስካቫተር cat ወይም hitachi; ከ340 ፈረስ ጉልበት በላይ የሆነ ሩሎ ባለ 12 ቶን cat ወይም liugong በመከራየት ጠጠር መንገድ ጥገና ማሠራት ይፈልጋል።
ስለዚህ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የመወዳደሪያ መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።
1. ተጫራቾች /ተወዳዳሪዎች/ ኩባንያ ማሽን ለማከራየት የሥራ ፍቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች /ተወዳዳሪዎች በጨረታው ለመወዳደር የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከሀገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት ወይም ከጉሙሩክ ባለሥልጣን ወይም ከፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት ማቅረብ አለባቸው። እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ 15% ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
3. ተፈላጊ የማሸን /ተሽከርካሪ /ዓይነት ከ2018 ወዲህ የተሠራና የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ ወይም ከማሽን አከራይ ድርጅት ሕጋዊ ወክልና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች; /ተወዳዳሪ/ ድርጅት የሥራ ልምድ ያለውን ኦፕሬተር ማቅረብ የሚችልና ኦፕሬተሩ ችግር ከፈጠረ መቀየር የሚችል መሆን አለበት።
5. ተጫራቾች በሥራላይ የሚያጋጥሙ ችግሮች ካሉ /የማሽኑ/ የተሽከርካሪው / ጥገና ወጪ በራሳቸው ለመሸፈን ዝግጁ የሆኑ።
6. መ/ቤቱ ለማሠራት ካወዳደረው መንገዶች ውስጥ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የማሠራት መብቱ የተጠበቀ ነው።
7. ተወዳዳሪ አሸናፊ ለሥራው የሚያስፈልጉትን ነዳጅ፣ ዘይት፣ ግራሶና ሌሎችንም ወጪዎች ራሳቸው ለመሸፈን ፈቃደኛ የሆኑ።
8. ተጫራቾች /የማሽኑን/ ተሽከርካሪውን ጭነው ማቅረብና ከሳይት ሣይት በራሳቸው ወጪማጓጓዝ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
9. ተጫራቾች ጨረታውን ተወዳድረው ካሸነፉ በ10 ቀናት ውስጥ /የማሽኑ/ የተሽከርካሪውን ወደሥራ ቦታ ለማስገባት ዝግጁ የሆኑ፡፡
10. ተጫራቾች ካሁን በፊት በዚህ ዓይነት ሥራ ላይ ተወዳድረው አሸንፈው ከሠሩበት መ/ቤት ከአንድ ዓመት ወዲህ የተሰጣቸውን የሥራ ጥራት የምስክር ወረቀት /የሥራ ልምድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
11. የተጫራቾች /የተወዳዳሪዎች/ ዋጋ ወይም ውጤት ተቀባይነት የሚያገኘው የተጠቀሱት ተፈላጊ ማሽኖች ጠቅላላ ዋጋ ተደምሮ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ተወዳዳሪ አሽናፊ ይሆናል፡፡
12. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ብር 50,000(ሀምሳ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከጨረታው ሠነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
13. ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ውል ሰምምነት ለመፈጸም ዘግጁ የሆኑ፡፡
14. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ማሽን በቂ ፐርፎርማንስ ሊኖረው የሚገባ መሆን አለበት፡፡ ከሚጠበቀው /standard/ በታች ከሆነ በሌላ ለመተካት ፈቃደኛ መሆን አለበት፡፡
15. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ቴክንካል፣ ኦሪጅናልና ኮፒ ፋይናንሻል ኦሪጅናልና ኮፒ በማሽግ የሚመለከተውን የድርጅቱን ኃላፊ በማስፈረምና ሕጋዊ ማህተም አድርገውበት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም የጨረታ ሣጥን ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
16. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ውስጥ የጨረታውን ሠነድ ከዲዴሣ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 600 (ስድስት መቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ15ኛው የሥራ ቀን በ11/3/2018 ዓ.ም በ6፡00 ሰዓት የጨረታ ሣጥን ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን በሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 09 20 36 03 88 / 09 13 37 42 37 ሁሌ በሥራ ሰዓት መደወል ይችላሉ።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በቡኖ በደሌ ዞን የዲዴሣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት