የሌቃ ዱላቻ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው መንገድና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት በወረዳው ካፒታል በጀት መንገድ ጥገና ስራ ለማሰራት የሚውሉ የግሬደር፣ የኤክስካቫተር፣ ሮለር፣ ሲኖ ትራክ እና ሻወር ትራክ ማሽኖችን በኪራይ ለመቅጠር ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 31, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 

የሌቃ ዱላቻ ፋይናንስ /ቤት ለወረዳው መንገድና ሎጀስቲክስ /ቤት በወረዳው ካፒታል በጀት መንገድ ጥገና ስራ ለማሰራት የሚውሉ የግሬደር፣ የኤክስካቫተር፣ ሮለር፣ ሲኖ ትራክ እና ሻወር ትራክ ማሽኖችን በኪራይ ለመቅጠር ይፈልጋል።

ስለዚህ የማሽነሪ ኪራይ ፈቃድ ያላችሁና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በጨረታው እንድትሳተፉ እናስታውቃለን፡፡

አስፈላጊ መስፈርቶች

1. የማሽነሪ ኪራይ ንግድ ፈቃድ 2018 . የታደሰ፤

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Number) ያላችሁና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆናችሁ፤

3. 2017/18 . ግብር መክፈላችሁን የሚገልጽ ከገቢዎች ባለስልጣን የሚቀርብ ደብዳቤ፤

4. ተጫራቾች የማሽኖቹን የምርት ስም፣ የተመረተበትን ሃገር፣ የሞዴል ቁጥር እና የተመረተበትን ዓመት በግልጽ በመጻፍ ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡

6. ለመንገድ ጥገና የሚውሉ ማሽኖች ዝርዝር፡

  1. ግሬደር ሞዴሉ 140H/K/G እና የፈረስ ጉልበቱ 185 እና በላይ የሆነ፣ የምርት ዓመቱ 2017 በፊት ያልሆነ፤
  2. ኤክስካቫተር ሞዴሉ CL/DL 325 እና በላይ የሆነ እና የፈረስ ጉልበቱ 318 እና በላይ የሆነ፣ የምርት ዓመቱ 2017 . በፊት ያልሆነ፤
  3. ሲኖ ትራክ ሞዴሉ 325 እና በላይ የሆነ፣ የፈረስ ጉልበቱ 336 እና በላይ የሆነ፣ የምርት ዓመቱ 2020 በፊት ያልሆነ፣ ክፍያው እንደ ርቀቱ (0-5 .ሜ፣ 5-10 .ሜ፣ 10-15 . እና 15-20 .) የሚከፈል ሲሆን ተጫራቾች ዋጋውን በዝርዝር መግለጽ አለባቸው፡፡
  4. ሮለር ሞዴሉ BW 14 AD እና ከዚህ በታች ያልሆነ የፈረስ ጉልበቱ 160 እና በላይ የሆነ፤
  5. ሻወር ትራክ ሞዴሉ 325 እና በላይ የሆነ የፈረስ ጉልበቱ 336 እና በላይ የሆነ የምርት አመቱ 2017 GC እና ከዚህ በፊት ያልሆነ፤

7. የባለቤትነት ማረጋገጫ (ሊብሬ) ማቅረብ የሚችሉ እና ማሽኑ ጉዳት ከደረሰበት በራሱ ወጪ በአስር (10) ቀናት ውስጥ መጠገን ወይም ተመሳሳይ ማሽን መተካት የሚችሉ።

8. የኪራይ ቦታ አድራሻ በአግባቡ የተረጋገጠ የወረዳ፣ ቀበሌ፣ የቤት ቁጥር እና ስልክ ቁጥር ማቅረብ አለባቸው፡፡

9. ተጫራቾች የዚህን ስራ ልምድ የሚያሳይ ማስረጃ 2015 . በፊት ማቅረብ አለባቸው (አዲስ ፈቃድ አይታሰብም)፡፡

10. ተጫራቾች እንደ ምግብና መጠጥ፣ ማረፊያ ቦታ፣ ማሽኑን በስራ ቦታ መጠበቅ፣ ነዳጅ እና ሌሎች ወጪዎችን በራሳቸው ይሸፍናሉ።

11. የማሽኖቹን የትራንስፖርት ወጪ (መጫንና ማውረድ) ተጫራቾች በራሳቸው ይሸፍናሉ።

12. ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችሉ ሲሆን የጨረታው አሸናፊ ከተለየ በኋላ በአምስት (5) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረጋል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾቹ የድርጅቱን ስነ ምግባር ካላከበሩ የጨረታ ማስከበሪያው ያለ ምንም ጥያቄ ለመ/ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡ እንዲሁም አሸናፊው ማሸነፉን ካወቀ በኋላ ማሽኑን በተስማማበት ጊዜ ካላቀረበ የጨረታ ማስከበሪያው እና የውል ማስከበሪያው ለመ/ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡

13. የውል ማስከበሪያው ከጠቅላላው ዋጋ 10% የሚያስይዝ ሲሆን የውል ማስከበሪያው ስራው ከተጠናቀቀ በኋላ ተረጋግጦ ርክክቡ ከተፈጸመ በኋላ ተመላሽ ይደረጋል፡፡

14. የጨረታው አሸናፊ በአካል ቀርቦ ውል መፈረም አለበት።

15. ተጫራቾች ለጨረታው የሚያስፈልገውን ሰነድ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) ብቻ ለወረዳ ሌቃ ዱላቻ ገቢዎች /ቤት የማይመለስ ክፍያ በመክፈል ከፋይናንስ /ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡

16. የመንገድ ጥገናው ጥራት ያለው እንዲሆን መንገድና ሎጀስቲክስ /ቤት ወይም የወረዳ አስተዳደር /ቤት በመከታተል የማስቆም መብት አለው፡፡

17. ለጨረታ የሚቀርብ ማንኛውም ሰነድ የተሰረዘ፣ የደፈረሰ ወይም ፎቶ ኮፒው የማይነበብ ከሆነ ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡

18. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በአራት (4) ፖስታዎች ማቅረብ አለባቸው፡፡

A. የቴክኒክ ፖስታ ዋናውና ኮፒው ለየብቻ በካኪ ፖስታ ተደርጎ በድርጅቱ ማህተም ተረጋግጦ በሁሉም ፖስታዎች ላይ ፊርማ ተደርጎ በአንድ ፖስታ መቅረብ አለበት፡፡

B. የፋይናንስ ፖስታ ዋናውና ኮፒው ለየብቻ በካኪ ፖስታ ተደርጎ በድርጅቱ ማህተም ተረጋግጦ በሁሉም ፖስታዎች ላይ ፊርማ ተደርጎ በአንድ ፖስታ መቅረብ አለበት፡፡

C. ሁሉም (የቴክኒክና የፋይናንስ ፖስታ በአንድ ትልቅ ፖስታ ተደርጎ በድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ተረጋግጦ በግዢ ክፍል መመዝገብና በግዢ ክፍል ውስጥ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

19. ይህ ጨረታ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን 400 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳ አስተዳደር ክፍል 430 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ሰነዳቸውን ካስገቡ በኋላ በጨረታው መክፈቻ ላይ ባይገኙም የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።

ማሳሰቢያ፦

  • ድርጅቱ የተሻለ ዋጋ ወይም ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ተጫራቾች በጨረታ መክፈቻ ላይ ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉልም፡፡
  • ሁሉም ፖስታዎች የድርጅቱን ስምና ስልክ ቁጥር መያዝ አለባቸው፡፡
  • ለተጨማሪ መረጃ 09-35-88-67-18/ 09-20-41_08-08/ 09 34-39-21-99 ስልክ ቁጥር መጠየቅ ይቻላል።

በወረዳው ካፒታል በጀት የተሸፈኑ የማሽኖች ኪራይ ዋጋ

የማሽኑ ዓይነት መለኪያ ብዛት የአንድ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ

1. ግሪደር ሰዓት 150

2. ኤክስካቫተር ሰዓት 150

3. ሻወር ትራክ ሰዓት 70

4. ሮለር ሰዓት 100

ጠቅላላ ዋጋ

.. (15%)

..ታን ጨምሮ ጠቅላላ ዋጋ

በወረዳው ካፒታል በጀት የተሸፈኑ የሲኖ ትራክ ኪራይ ዋጋ

. የማሽኑ ዓይነት መለኪያ የጊዜ ልዩነት በኪ. ብዛት የአንድ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ

  • 1 ጭነት መኪና (D/truck) ባጆ 0-5. 250
  • 5-10 .
  • “” 10-15 .
  • “”15-20 .
  • ጠቅላላ ዋጋ

የሌቃ ዱላቻ ፋይናንስ /ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *