Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመጋዘን ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል
Addis Zemen(Jan 23, 2026)
በድጋሚ የወጣ የመጋዘን ኪራይ አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር NEBE/NCB/RE/001/2018
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኝ ብዛት ሁለት መጋዘን እያንዳንዱ የግቢው ስፋት ቢያንስ 2500 ካሬ የሆነ እና የመጋዘን ስፋት ቢያንስ 2200 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ለአስር ወር በሚቆይ ሆኖ እንደሁኔታው ሊራዘም የሚችል በውል ስምምነት ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 እና ከ7፡30 እስከ 11 30 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከቦርዱ ግዥ ስራ ከፍል ቢሮ ቁጥር 107 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስና የዘመነ ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ምዝገባ ምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እንዲሁም በመንግሥት የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ድህረ–ገጽ የአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱን ከቦርዱ ዋና መስሪያ ቤት የግዥ አስተዳደር የስራ ክፍል በመውሰድ ሞልተው አግባብ ባለው አካል በመፈረም ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን የቴክኒክና የዋጋ ሰነዳቸውን ኦርጅናልና ኮፒ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለአንድ መጋዘን መጫረት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለአንድ መጋዘን ለጨረታ ማስከበሪያነት ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ለሁለት መጋዘን ለጨረታ ማስከበሪያነት ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ቦርዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ ካለው ዋና መ/ ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ
አድራሻችን፡- ቦሌ ፍላሚንጎ ካፌ ገባ ብሎ ስልክ ቁጥር፡- +251 115153468
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ