የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በስሩ ያሉትን ለተለያዩ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን ለማከራየት ስለፈለገ፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል


Addis Zemen(Jan 24, 2026)

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 71

የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በስሩ ያሉትን ለተለያዩ ፓርኮች ማለትም የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በውስጡ የሚያስተዳድራቸው በኮሪዶር ልማት የለሙ ፓርኮች ውስጥ ሽሮ ሜዳ አካባቢ፣ ፉሪ፣ ጀርመን አደባባይ፣ ሾላ አካባቢ፣ ሰንጋ ተራ፣ አትሌት ፌዴሬሽን አካባቢ፣ ስድስት ኪሎ አካባቢ፣ መካኒሳ፣ ገርጅ ኦቪድ ሪል ስቴት አካባቢ በአራት ኪሎ ፕላዛ (Underpass) ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን ለማከራየት ስለፈለገ፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል።

በመሆኑም የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ተጋብዘዋል።

1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለበት።

2. ፓርኮቹ ውስጥ ገብቶ ለመስራት ፍቃደኛ የሆነና ከተቋማችን ጋር ውል ገብቶ በገበያ ጥናት እና የመነሻ ዋጋ መሰረት ተወዳድረው አስፈላጊውን ክፍያ የሚከፍልና በውሉ መሰረት ግዴታውን መወጣት የሚችል።

3. በግቢ ያሉ ፋውንቴኖችንና፣ መናፈሻዎችን፣ የመጸዳጃ ቤቶችን፣ የጽዳት፣ የጥበቃ፣ የተለያዩ ጥገናዎችን ከሌሎች ተከራዮች ጋር በመሆኑ ማስጠገን ፣ መቆጣጠርና በአግባቡ ማስተዳደር የሚችል።

4. ለህዝብ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተመጣጣኝ የገበያ ዋጋ ለማቅረብ ፍቃደኛ የሆነ።

5. ኮርፖሬሽኑና የከተማ አስተዳደሩ በሚወጣው የስራ ሰአት፣ ቅዳሜ እና እሁድ ፣ በአላትን እንዲሁም ምሽትን ጨምሮ አገልግሎት መስጠት የሚችል።

6. አሸናፊነት ከታወቀ በኋላና ውል ከወሰደ በኋላ በ3 ቀን ውስጥ ስራ መጀመር የሚችል።

7. ስታንዳርዱን የጠበቀ እና የኮሪዶር ልማቱን የሚመጥን እቃዎችን ይዞ መግባት የሚችል።

8. ከተቻለ በሬስቶራንት ፣ በካፌ እና ህዝብ መዝናኛ ፓርክ ላይ ልምድ ያለውና መረጃ ማቅረብ የሚችል

9. ተጫራቾች 50000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

10. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ መገናኛ ዘፍመሽ ፊት ለፊት ታሜጋዝ ህንጻ ላይ ሶስተኛ ፎቅ የፋይናንስ ዳይሬክትሬት ቢሮ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር ተከታታይ የስራ ቀን ከጠዋት 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይቻላል።

የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *