የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን (GC-1) በጨረታ አወዳድሮ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የደህንነት አጥር ፕሮጄክት የCCTV፣ IDS እና የኤሌክትሪክ መብራቶች ዲዛይን፣ ገጠማ፣ ሙከራ እና ኮሚሽኒንግ አገልግሎት ለማሠራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Jan 30, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር SSNT-1595

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን (GC-1) በጨረታ አወዳድሮ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የደህንነት አጥር ፕሮጄክት የCCTVIDS እና የኤሌክትሪክ መብራቶች ዲዛይን፣ ገጠማ፣ ሙከራ እና ኮሚሽኒንግ አገልግሎት ለማሠራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ለሥራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች፣ የዘመኑን የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከተፈቀደለት አካል በምድብ GC-1፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ, (PAA) የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ በመንግሥት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነፃ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT T595 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ከፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 / አምስት መቶ ሺህ ብር/ በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም ለ150 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጨረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ማክሰኞ የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ9:00 ሰዓት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517-8025
ኢ-ሜይል: KidistTa@ethiopianairlines.com 
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።