ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ የጽህፈት መሳሪያ መገልገያ፣ የፕሪንተር ቀለም እና የኮፒ ማሽን ቀለም ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Jan 31, 2026)

ብሄራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

  1. ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት በአገር ውስጥ የሚፈፀሙ ለኢንዱስትሪ መገልገያ አገልግሎት የሚውሉ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ በስሩ ላሉት ሰራተኞች አጠቃላይ የጽህፈት መሳሪያ መገልገያ የፕሪንተር ቀለም እና የኮፒ ማሽን ቀለም ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
  2. ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትጫረቱ ተጋብዟችኋል።
  3. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
  4. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።
  6. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
  7. ተጫራቾች በኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስም በብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሎት -1- የጽህፈት መሳሪያ መገልገያ እቃዎች 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ለሎት -2 – የፕሪንተር እና የኮፒ ማሽን ቀለም 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ለየብቻው ከሰነድ ጋር በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርበታል።
  8. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል መሙላትና በማህተም ማረጋገጥ አለበት።
  9. ተጫራች የሚያቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት።
  10. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ አንደኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል ሰነዱን በሶፍት ኮፒ መግዛት ይችላሉ።
  11. ተጫራቾች በገዙትና በሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፁትን ሁኔታዎች በአግባቡ በመጠቀም የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ ኤንቨሎፕ አሽገው 2ኛ ፎቅ ላይ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  13. ተጫራች ለጨረታ ሰነዱ ቴከኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዱን ለየብቻ ለይተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  14. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ይዘጋል በዚሁም ዕለት ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3ኛ ፎቅ ላይ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  15. የጨረታው መዝጊያና መካፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
  16. ጨረታው የሚፀናበት ጊዜ 60(ስልሳ) ተከታታይ ቀናት ስለሆነ ተጫራቾችም ይህንኑ አውቀው ስለመቀበላቸው በቴክኒካል ኦርጅናል ሰነዳቸው ላይ ማረጋገጥ አለባቸው።
  17. ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም፣ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡-ለቡ መብራት ኃይል ከጀነራል መርከንታይል አጠገብ

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥራችን ስልክ: +251 92 495 5389 +251 91 016 2733 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ

ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *