Your cart is currently empty!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የከተማው ማዘጋጃ ቤት ህንፃ ማስፋፊያ ግንባታ ግዥ ለማድረግ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ባላቸው በደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ በሆኑ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 02, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር-006/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የከተማው ማዘጋጃ ቤት ህንፃ ማስፋፊያ ግንባታ ግዥ ለማድረግ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ባላቸው በደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ በሆኑ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
1- ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ (ከሊራንስ) ማቅረብ የሚችሉ።
2- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑና ስለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /IIN NUMBER/ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3- ተጫራቾች በፌዴራል መንግስት የግዥ ስርዓት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና e-GP ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
4- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ፤ CPO 60,000 (ስልሳ ሺ ብር) በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከወ/ጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ግ/ን/አስ/ዋና/ስራ/ሂደት ክፍል ቀርቦ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
6- ተወዳዳሪዎች የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰአት የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
7- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ሁለት ኮፒውን በተናጠል ለይቶ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8- ተወዳዳሪዎች የደረጃ ፍቃድ እና ማደሳቸውን የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ማሳሰቢያ
1ኛ/ማንኛውም ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ከዋጋ ጥናት መረጃ ጋር 15% ከፍ የሚል ከሆነ ውድቅ ይደረጋል።
2ኛ/ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው ኮሚቴ ጨረታው ሊከፍት ይችላል።
3ኛ/ ከዋጋ ጥናቱ ከ15% በታች በሆነ ዋጋ ጨረታ የሚያሸንፍ ተወዳዳሪ ያለቅድመ ክፍያ ስራ ይጀምራል። እንዲሁም የውል ማስከበሪያ 20% የሚያሲይዝ መሆኑን እንገልፃለን። በተጨማሪም ማስያዣ (ሪቴንሽን) 7% መሆኑን እንገልፃለን።
4ኛ/ በተደረገው የሂሳብ ስህተት ማስተካከያ (Arithmetic Error) የመጣው ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ መክፈቻ ስነ- ስርዓት ላይ ከተነበበው ጠቅላላ ዋጋ ከ5% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ ከሆነ የተወዳዳሪው ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
5ኛ/ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
6ኛ/ መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ ቤት
ጽ/ቤት