Your cart is currently empty!
በአብክመ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች እና ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 02, 2026)
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብከመ የሙያ ብ/ም/ማ ኤጀንሲ የደ/ማ/ክ ማዕከል ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች እና ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. በዘመኑ የታደሰ በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
2 የዘመኑን ግብር የከፈሉ
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው
4. የግዥው ጠቅላላ መጠን ዋጋ ብር 200000.00 /ሁለት መቶ ሺህ / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ
5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁጥር ከ1- 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
6 የሚገዙ እቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ በፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከዋና ገ/ያዥ ላይ ብር 100.00 /አንድ መቶ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።
8.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ዋና ገንዘብ ያዥ ላይ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ኮፒ በፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደ/ማ/ሙ/ብ/ም/ማከማዕከል ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 5፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት 16ኛው ቀን በ 8፡00 ሠዓት ይከፈታል፡፡ ካልተገኙም በኮሚቴው ይከፈታል ። ነገር ግን 16ኛው ቀን የበአል ቀን ከሆነ በአቱ እንደተጠበቀ የጨረታ ማስገቢያና መክፈቻ ቀን በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል።
11. ተጫራቾች ከላስተሩ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የእቃውን ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከተቀመጠው ስፔስፊኪሽን ውጪ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም።
12. የጨረታው ውድድር የሚታየው ከላስተሩ ባወጣው ዝርዝር መሰረት በጥቅል ዋጋ በሎት ይሆናል።
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከሪም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. በጨረታ የሚሳተፉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁ/ 058 178 10-73 / 058 178 71 46 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ። ቢሮአችን ደ ማርቆስ ከተማ አምባሰል ህንጻ 5ተኛ ፎቅ ላይ ይገኛል።
በአብክመ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና
ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል