Your cart is currently empty!
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የፅዳት እቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች እና የስራ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 03, 2026)
የግዥ ግልፅ የጨረታ
ማስታወቂያ
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
- ሎት አንድ: የፅዳት እቃዎች
- ሎት ሁለት: የፅህፈት መሳሪያዎች እና
- ሎት ሶስት: የስራ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የግብር መክፈያ ግዴታቸው የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥና በግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ቅጂ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ከላይ የተሰጡት እና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ኦርጂናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከመከፈቱ በፊት ናሙና ይዘው ማቅረብ የሚችሉና የስራ ልብሱ በምናቀርበው ናሙና መሰረት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ለእያንዳንዱ ሎት (lot) የቀረበው ዋጋ ቢያንስ ለጨረታ ዋስትና ሎት-1 ብር 35,000 ( ሰላሳ አምስት ሺህ) ፤ ሎት-2 ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር)፣ ሎት ሶስት 50,000 (አምሳ ሺህ ብር) በአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስም አዘጋጅቶ የጨረታ ዋስትና ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመከፍል የጨረታው ሙሉ ሰነድ በኢንዱስትሪው ግዥ ከፍል ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ።
- መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳችሁን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት እስከ አስራስድስተኛው ቀን 8፡00 ድረስ ብቻ ማስገባት ትችላላችሁ።
- ጨረታው ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት እየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በአስራ ስድስተኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ 8:00 ተዘግቶ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
አድራሻ፡- በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዲስ ማሽንና እና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሣር ቤት በሚወስደው መንገድ ከአይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ ያለው ግቢ
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና
መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ