Your cart is currently empty!
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት በአገር ውስጥ የሚፈፀሙ በኢንዱስትሪው ስር ላሉት አጠቃላይ ተሽከርካሪዎች ጥገና (service) የአገልግሎት ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 03, 2026)
ብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት በአገር ውስጥ የሚፈፀሙ በኢንዱስትሪው ስር ላሉት አጠቃላይ ተሽከርካሪዎች ጥገና (service) አገልግሎት ግዥ
- የአገልግሎት ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትጫረቱ ተጋብዟችኋል።
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin) ማስረጃ ማቅረብ አለበት
- ተጫራቾች በኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስም በብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት 50.000 (ሃምሳ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ለየብቻው ከሰነድ ጋር በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል መሙላትና በማህተም ማረጋገጥ አለበት።
- ተጫራች የሚያቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት።
- ተጫራቶች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢከፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ አንደኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል ሰነዱን በሶፍት ኮፒ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በገዙትና በሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፁትን ሆኔታዎች በአግባቡ በመጠቀም የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ ኤንቨሎፕ አሽገው 2ኛ ፎቅ ላይ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራች ለጨረታ ሰነዱ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዱን ለየብቻ ለይተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ይዘጋል በዚሁም ዕለት ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3ኛ ፎቅ ላይ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
- ጨረታው የሚፀናበት ጊዜ 60 (ስልሳ) ተከታታይ ቀናት ስለሆነ ተጫራቾችም ይህንኑ አውቀው ስለመቀበላቸው በቴክኒካል ኦርጅናል ሰነዳቸው ላይ ማረጋገጥ አለባቸው።
- ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም። ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ፡- ለቡ መብራት ኃይል ከጀነራል መርከንታይል አጠገብ
- ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥራችን ስልክ: +251 924955389 +251 910162733 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ