ክርስቲያን ሆራይዘንስ ኢትዮጵያ (Christian Horizons Ethiopia ) እ.ኤ.አ ከ January 1,2025 እስከ December 31,2025 ድረስ ያለውን የሂሳብ እንቅስቃሴ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 03, 2026)

ለኦዲት ሥራ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ክርስቲያን ሆራይዘንስ ኢትዮጵያ (Christian Horizons Ethiopia ) የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን መ/ቤት በምዝገባ ፍቃድ 1045 ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በአርሲና በባሌ ዞኖች አንዲሁም በአሰላ ከተማ ውስጥ በርካታ የልማትና የርዳታ ሥራዎችን በመሥራት ላይ የሚገኝ መንግሥታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል በጎ አድራጊ ድርጅት ነው።

በዚሁ መሠረት ለሚመለከተው የመንግሥት ባለድርሻ አካላት እ.ኤ.አ ከ January 1,2025 እስከ December 31,2025 ድረስ ያለውን የሂሳብ እንቅስቃሴ ኦዲት ማስደረግ ስለምንፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የኦዲት ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1) የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው

2) የሙያ ማረጋገጫ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ

3) ከኢትዮጵያ አካውንቲንግ እና ኦዲቲንግ ቦርድ (AABE) የታደሰ የሙያ ፍቃድ ያለው/ ያላት

4) የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ

5) ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ

አመልካቾች ሥራውን ለመሥራት የሚያስከፍሉትን ዋጋ እና ሥራውን ሠርተው የሚያጠናቅቁበትን ጊዜ በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስምንት (8) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ መሠረት አስፈላጊውን መረጃ በማያያዝ ትልኩልን ዘንድ በአክብሮት እንገልፃለን ፡፡

አድራሻ፡-
ፖስታ ሳጥን ቁጥር 370 አርሲ አሰላ
ስልክ ቁጥር ፡ 09 11 36 60 53/ 09 11 15 94 28
tewabhabt@gmail.com 
ክርስቲያን ሆራይዘንስ ኢትዮጵያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *