የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና /ኢኮ/ልማት መምሪያ የተለያዩ የእንስሳት መድኃኒትና ቁሳቁሶች ግዥን ለመፈጸም በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 03, 2026)

 ጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና /ኢኮ/ልማት መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ እንስሳት ሀብት ልማት መምሪያ የተለያዩ የእንስሳት መድኃኒትና ቁሳቁሶች ግዥን ለመፈጸም ያስፈለገ መሆኑ በ2018 በጀት ዓመት በታቀደው መሠረት በዘርፉ ፈቃድ ካለው ድርጅት መካከል በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት:

  1. በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው ማኅበራት፤-
  2. በሥራ መስኩ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
  3. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
  4. በጨረታው እንዲሳተፍ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤
  5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ሕንፃ ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ በብር 300(ሶስት መቶ ብር) በመግዛት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ የተረጋገጠ /የተመሰከረ/ ሲፒኦ CPO ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰንድ ጋር ማቅረብ አለበት
  7. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናልና እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ እና ከላይ የተጠቀሱትን ቴክኒካል ቅድመ ግምገማ ሰነዶችን አሟልቶ በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8.  ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል ፡፡
  9.  መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር 046-212-13–34

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና/ኢኮ/ልማት/መምሪያ

/ሀዋሳ/


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *