Your cart is currently empty!
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት የኮንስትራክሽን ላብራቶሪ ዕቃዎች እና የጽህፈት መሣሪያ ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 03, 2026)
ለሁለተኛ ዙር የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት
- የኮንስትራክሽን ላብራቶሪ ዕቃዎች እና
- የጽህፈት መሣሪያ ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላችው፣ ቫት ተመዝጋቢ፣ ዓመታዊ የስራ ግብር የከፈሉ እና በፋ/ኢ/ል/ቢሮ(በፋ/ኢ/ሚኒስቴር) በክልሉ ገቢዎች ቢሮ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘረውን የእያንዳንዱን ዋጋ ሞልተው፣ ፈርመው እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የላብራቶሪ ፋይናንሻል ኦርጅናል አንድ ፎቶ ኮፒ እና ቴክኒካል ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ ለብቻ ለብቻ እና የስቴሽነሪ አንድ ፋይናንሻልና አንድ ፎቶ ኮፒ የስቴሽኔሪ ሲፒኦ በፋይናንሻል ኦርጅናል ዶክሜንት ጋር በማሸግ የሁሉም ዶክሜንቶችን ለብቻ ለብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኮን/ባለስልጣን ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በመምጣት የጽህፈት መሣሪያ ሰነድ በ300/በሶስት መቶ ብር እና የላብራቶሪ ሰነድ በ400/አራት መቶ ብር በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት /CPO/ለላብራቶሪ 150,000/አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክሜንት ላይ አንድ ጋር በማሸግ እና ለስቴሽኔሪ 8,000/ ስምንት ሺህ ብር ከፋይናንሻል ኦርጅናል ዶክመንት ጋር አሽጋችሁ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ወዲያውኑ ተጫራች /ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 6፡00 ታሽጎ 8፡ዐዐ ይከፈታል።
- ተጫራቾች በተወዳደሩበት የዕቃ አይነት የአሸናፊነት ደብዳቤ እንደደረሳቸው መ/ቤት በመምጣት በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ጋራንቲ በማስያዝ ከቢሮው ጋር ውል መግባት አለባቸው።
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን የዕቃ አይነት ዕቃውን በራሱ ማጓጓዣ ቢሮ ድረስ በማቅረብ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለበት ውሉን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ባይፈራረም የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበርያ ያስገባው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ስትሞሉ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ መሆን አለበት ካልሆነ ውድቅ ይደረጋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር መስፍርቶችን ከጨረታ ሰነዱ መረዳት ይቻላል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-11-74-74-93/ 09-16-03-50-70/ 09-04-82-92-69
አድራሻ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ቡታጅራ ከተማ ችግኝ ጣቢያ አጠገብ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን