Your cart is currently empty!
የቦሌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የደንብ ልብስ፣ አላቂ ጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ ጥገና እና ህትመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 02, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የቦሌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በቁጥር 002/2018 ዓ.ም የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የደንብ ልብስ 1000 ብር የጨረታ ማስከበሪያ
- ሎት 2 አላቂ ጽህፈት መሳሪያዎች 2100 ብር የጨረታ ማስከበሪያ
- ሎት 3 አላቂ የፅዳት ዕቃዎች 2500 ብር የጨረታ ማስከበሪያ
- ሎት 6 ጥገና 2000ብር የጨረታ ማስከበሪያ
- ሎት 7 ህትመት 2000 ብር የጨረታ ማስከበሪያ
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- በሚጫረቱበት ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር እቃ አቅራቢዎች የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ ሆነው ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋም ካደራጃቸው አካል የአምራችነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በምድብ 1፣2፣3፣6፣7 የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት በተቋቋሙበት የንግድ ዘርፍ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች በዝርዝሩ መሰረት ዋጋ ሞልተው የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናልና ኮፒ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሰነዱ ታሽጎ ባይቀርብና ተፈላጊ ሰነዶች ቢጎድሉ ኃላፊነቱ የተጫራች ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በየሎቱ ላይ በተገለፀው መሰረት እያንዳንዱ የሎት ዋጋ ብር በባንክ በተመሰከረ /ሲፒኦ/ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ብዛቱ ሊጨምርም ሆነ ሊቀንስ የሚችለው 20% ነው።
- አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን ዋጋ 10% በሲፒኦ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
ማንኛውም ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ እስከ 11፡00 ሰዓት ማስገባት የሚችል ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻና መዝጊያ በስራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥሉት የስራ ቀን ይሆናል፡፡ ለእያንዳንዱ ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ቁሳቁሶች ሳምፕል / ናሙና/ ከነማብራሪያው ከጨረታ ዶከመንት ጋር አብሮ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ሳምፕል ያላቀረበ ተጫራች ከውድድር ውጭይሆናል፡፡ ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መ/ቤቱ ባቀረበው እስፔሲፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስ.ቁ. 0116393119
አድራሻ፡- ከቦሌ ከመድሐኒአለም ቤተክርስቲያን ወደ 22 ማዞሪያ በሚወስደው መንገድ አለምነሽ ፕላዛ ህንፃ ፊት ለፊት
የቦሌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Furniture cttx, cttx House and Building cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Office Machines and Computers cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Others cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx