Your cart is currently empty!
የቦታው ስፋት በካርታ 343 ካ/ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Feb 03, 2026)
በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ወ/ሪት መሰረት ያረጋል እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ የኔነሽ አመራ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 181391 በ3/4/2015 ዓም እና መ/ቁ/187591 በ28/4/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 5 የቤ.ቁ/1040 የሆነው ቤት ፍርድ ያረፈበት ቤት በካርታ ቁጥር 07/42/13005/00 የተመዘገበ ካርታ ያለው የቦታው ስፋት በካርታ 343 ካ/ሜ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 10,410,354(አስር ሚሊዮን አራት መቶ አስር ሺህ ሶስት መቶ ሃምሳ አራት ብር) ሆኖ በጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል የሚል ማስታወቂያ ወጥቶ በእለቱ ተጫራች አልቀረበም። ይህንኑ ለፍ/ቤቱ ሪፖርት ተደርጎ ፍ/ቤቱ በ14/4/2018 ዓ/ም በድጋሚ ጨረታ እንዲወጣ ትዕዛዝ የሰጠ በመሆኑ በሁለተኛ ጨረታ የሚያዘው 1/4ኛ ብር 2,602,588.5 (ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ሰማኒያ ስምንት ብር 5/100) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ የካቲት 27 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትናባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሽጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
በፌዴርል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት