በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሻሁራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የኮብል እስቶን መንገድ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


Be’kur(Feb 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሻሁራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የኮብል እስቶን መንገድ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ከሆኑ በጨረታዉ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ ጠቅላላ ወይም የህንፃ ግንባታ ሥራ ተቋራጭ GC/BC ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  4. የታደሰ የግንባታ ሙያዊ የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  6. የጨረታዉ ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ሚወዳደሩት ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
  7. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-6 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የሥራ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ሻሁራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ከግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ዘወትር በስራ ሰዓት ከጥር 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 15/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ድረስ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ጨረታው ከወጣበት እለት ከጥር 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 16/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዳቸዉን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ እለት የጨረታ ሳጥኑ ከረፋዱ 4፡01 ታሽጎ 4፡15 ላይ ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ድምር 1.5 አንድ ነጥብ አምስት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሆነ በሌሉበት ሰነዱ ተሟልቶ ከተገኘ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቾች በራሳቸዉ ምርጫ ጨረታዉ በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ የጨረታ ሰነዱ እንዲከፈት ተደርጎ ያልተገኙ ተጫራቾች በእለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  14. ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከጽ/ቤቱ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 09 52 59 27 /09 24 25 89 41 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የሻሁራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *