Your cart is currently empty!
በምዕራብ ጎጃም ዞን በደጋ ዳሞት ወረዳ የፈረስ ቤት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 በጀት አመት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Be’kur(Feb 02, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ጎጃም ዞን በደጋ ዳሞት ወረዳ የፈረስ ቤት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 በጀት አመት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት2. ወረቀትና የወረቀት ውጤቶችን፣ ሎት3. የህንጻ መሳሪያ፣ ሎት4.ኮምፒውተርና የኮምፒውተር ተዛማጅ እቃዎችን፣ ሎት5. የጽዳት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
3. የሚያቀርቡት እቃ ከ200,000 ሽህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
4. የሚገዙት እቃዎች ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃው ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. ለእቃዎቹ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በፈረስ ቤት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን/ ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ጨረታው በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፈረስ ቤት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በ16ኛው ቀን በ3፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
8. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃ ከተቋሙ ንብረት ክፍል ማድረስ የሚችል መሆን አለበት፡፡
9. ከጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡
10. ጨረታው የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
11. ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ጥቅል ዋጋ ነው፡፡
12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 50 (ሀምሳ ብር ብቻ) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት ይችላሉ፡፡
13. በማስታወቂያው ያልተገለጸ ካለ በግዥ መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ከሎቶች ውስጥ አንዱን እቃ ካልሞሉ ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
14. ተጫራቾቹ በሰነዱ ላይ የድርጅቱን ስም ፣ማህተም ፣ፊርማ እና አድራሻ አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
15. የጨረታው አሸናፊ ውሉን ከወሰደበት ቀን ጀምሮ እቃዎችን በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
17. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በፈረስ ቤት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመቅረብ ወይም በ09 12 79 78 12 /09 2077 22 08 /09 10 67 87 33 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የፈረስ ቤት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ