Your cart is currently empty!
በጎንደር ከተማ አስተዳደር የብላጅግ ዳብርቃ ጤና ጣቢያ ለእናቶችና ህፃናት አገልግሎት የሚውል የተቋረጠ ግንባታ ለማስጨረስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Be’kur(Feb 02, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በጎንደር ከተማ አስተዳደር የብላጅግ ዳብርቃ ጤና ጣቢያ ለእናቶችና ህፃናት አገልግሎት የሚውል የተቋረጠ ግንባታ ለማስጨረስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት መጫረት የምትችሉ የህንፃ ተቋራጮች፡-
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- እሴት ታክስ (የቫት) ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- ሁሉም ተጫራቾች የመልካም ሥራ አፈፃጸም መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በከተማ ልማት የግንባታ የምስከር ወረቀት ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ የሙያ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ንግድ ፈቃዱን፣ የግብር ከፋይ መለያ፣ ቲን ነበር ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ፖስታው ላይ ስም፣ ፊርማና ማህተም መኖር አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብላጅግ ጤና ጣቢያ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ባሉት የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ በጥሬ ገንዘብ ካስያዙ ከጤና ጣቢያው ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ኮፒ ከፖስታው ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቹ የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ብላጅግ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 12 ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት አስከ ቀኑ 10፡30 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሀ እለት ከቀኑ 10፡30 ታሽጎ በ22ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋው ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመከፈቻ ቀኑ በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- የስራው ዝርዝር ወይም ስፔስፊክሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲ ሆን ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ምድብ ነው፡፡
- በጨረታው ላይ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በ09 18 41 92 90 /09 18 41 38 41 ደውለው መጠየቅ ወይም ብላጅግ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር በመምጣት መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የብላጅግ ጤና ጣቢያ