አያት አክሲዮን ማህበር ለሚገነባቸው የቤት ፕሮጀክቶች የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ የቤት ውስጥ ማጠናቀቂያ ቁሳቁሶችን (Finishing Materials) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Reporter(Feb 04, 2026)

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፦ AYAT/PPD/003/2018

ድርጅታችን አያት አክሲዮን ማህበር ለሚገነባቸው የቤት ፕሮጀክቶች የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ የቤት ውስጥ ማጠናቀቂያ ቁሳቁሶችን (Finishing Materials) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሚፈለጉ እቃዎች ዝርዝር

.

የዕቃው ዓይነት (Description)

መለኪያ

ብዛት (Quantity)

1

የወለል ሴራሚክ (60x60x8mm)

ካሬ ሜትር

223,031.57

2

የወለል ሴራሚክ (30×30×8 mm)

ካሬ ሜትር

402,078.17

3

የግድግዳ ሴራሚክ (60×30×6 mm)

ካሬ ሜትር

471,061.37

4

SPC ወለል

ካሬ ሜትር

751,169.97

5

ስከርቲንግ (Skirfing 10 cm height)

ሜትር

319,336.91

6

SPC የሚሆን ስከርቲንግ

ሜትር

799,547.83

የመወዳደሪያ መስፈርቶች እና መመሪያዎች

1. ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶችነ ለመስጠት ፍላጎት ፤ ብቃት እና ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች ከመገናኛ ወደ ካራ በሚወስደው መንገድ ወሰን ሚካዔል ትራፊክ መብራት አጠገብ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ግዥ መመሪያ ሦስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 311 ድረስ በመቅረብ ከጥር 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የተዘጋጅውን የጨረታ ሠነድ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል እስክ የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ መግዛት ይቻላሉ::

2. ህጋዊ ሰነዶች፦ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የቫት (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. የጨረታ ማስከበሪያ፦ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በአያት አክሲዮን ማህበር ስም አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

 4. የዋጋ ማቅረቢያ፦ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ወይም ተመሳሳይ ይዘት ባለው ፎርም ላይ በመሙላት እስከ የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም* ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

5. ናሙና (Sample)፦ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የቁሳቁስ ዓይነት ጥራት የሚገልጽ ናሙና ከጨረታ ሰነዱ ጋር የማቅረብ ግዴታ አለባቸው::

6. የጨረታ አከፋፈት፦ ጨረታው በተዘጋበት ዕለት (የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም) ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል አካባቢ በሚገኘው የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መሥሪያ ቤት ይከፈታል፡፡

7. መብት፦ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፦
ስልክ: +251-115514699 / +251-116463445 አያት አክሲዮን ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *