ኢኮስኮ ራይዚንግ ሆንግፋ ኃ.የተ.የግል ማህበር የተሽከርካሪ አሮጌ ባለሽቦ ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Reporter(Feb 04, 2026)

የጨረታ ቁጥር 04/2018 የጨረታ ማስታወቂያ

ኢኮስኮ ራይዚንግ ሆንግፋ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለጎማ መልሶ መጠቀም ፋብሪካ ጥሬ ዕቃ የሚሆን 11X20 እና/ወይም 12X20 የሆነ የተሽከርካሪ አሮጌ ባለሽቦ ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

.

እቃ አይነት

መለኪያ

ብዛት

ጨረታ ማስከበሪያ መጠን በብር

1

 

ባለ11×20 እና/ወይም ባለ12 x 20 የተሽከርካሪ አሮጌ ባለሽቦ ጎማ

በቁጥር

 

5,000

 

5,000 /አምስት ሺህ ብር/

 

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ::

1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ አግባብነት ያለው እና የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በተለምዶ ውሃ ልማት ተብሎ በሚጠራው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢኮስኮ ራይዚንግ ሆንግፋ ኃ/የተ/የግል ማህበር ዋና መ/ቤት GW ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 መውሰድ ይችላሉ::

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የባንክ ዋስትና ከሆነ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ30 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል::

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ ከታች የጨረታ መዝጊያ ተብሎ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከታች የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በግል ማህበሩ ዋና መ/ ቤት ይከፈታል::

6. የግል ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

የጨረታው መዝጊያ ቀን፡- የካቲት 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ቀን፡- የካቲት 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሠዓት

ኢኮስኮ ራይዚንግ ሆንግፋ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
ዋና መ/ቤት GlW ህንፃ 2ኛ ፎቅ
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡ +251917832984 /251910614251


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *