Your cart is currently empty!
ኦሮሚያ ባንክ ለጥበቃ ሰራተኞቹ የተለያዩ የደንብ ልብሶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Reporter(Feb 04, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡OT/14/2025-26
የደንብ ልብስ ግዥ ግልጽ ጨረታ
ኦሮሚያ ባንክ ለጥበቃ ሰራተኞቹ የተለያዩ የደንብ ልብሶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በሥራ ዘርፉ የተሰማራችሁ ዴርጅቶች ከታች በሰንጠረዥ ውስጥ የተገለጹ የደንብ ልብሶችን ለማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
|
ተ.ቁ |
ዝርዝር |
መለኪያ |
ብዛት |
መግለጫ |
|
1 |
ጃኬት |
በቁጥር |
613 |
በተለያየ ልኬት (Size) |
|
2 |
ሸሚዝ (ለወንዶች) |
በቁጥር |
1,178 |
በተለያዩ ልኬቶች (Size) |
|
3 |
ሸሚዝ (ለሴቶች) |
በቁጥር |
48 |
|
|
4 |
1ኛ ደረጃ ቴትሮን 6000 ብትን ጨርቅ |
በሜትር |
1,839 |
|
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1,000.00 (ብር እንድ ሺህ) በባንኩ ዋና መ/ቤት ሕንፃ ስር በሚገኘው የባንኩ አፍሪካ ጎዳና ቅርንጫፍ በመክፈል ከታች ከተጠቀሰውአድራሻ ክጥር 28 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ የጨረታ ሰነድ በመግዛት መሣተፍ ይችላሉ።
አድራሻ
ግዥ አስተዳደር ዋና ክፍል
የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ዘጠነኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 9-002
ቦሌ መንገድ ከጌቱ ንግድ ማዕከል አጠገብ
ስልክ ቁጥር 011 557 2098/95
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ከናሙና ጋር እስከ የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተገለፀው አድራሻ ለዚሁ አላማ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በተመሣሣይ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኦሮሚያ ባንክ