ዜጎች ለዜጎች የልማት ድርጅት የ2025 በጀት አመት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ካላቸው የኦዲት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስመርመር ይፈልጋል


Be’kur(Feb 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ23

ዜጎች ለዜጎች የልማት ድርጅት የ2025 በጀት አመት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ካላቸው የኦዲት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስመርመር ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉት ማሳሰቢያዎች በመከተል የሂሳብ ምርመራ ፈቃድ ያላቸው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡

  1. ተጫራቾች በፊደራል ወይም በክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የተሰጠ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. ተጫራቾች በሥራዉ ላይ የሚያሳትፋቸዉን ባለሙያዎች ብዛት የትምህርት ደረጃ የሥራ ልምድ ከእያንዳንዱ ባለሙያ ጋር የተፈራርሙትን የቅጥር ዉል ኮፒ ወዘተ የሚያቀርቡ፡፡
  3. ተጫራቾች ስለ መልካም ሥራ አፈጻጸማአቸዉ ከአሁን በፊት የሂሳብ ምርመራ ኦዲት ካደርጉባችው ድርጅቶች የተጻፈላችዉን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በሃርድ ዊር እና በሶፍት ዊር ሪፖርት ማድረግ የሚችል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከመስሪያ ቤቱ ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. አሽናፊዉ ድርጀት የሚለየዉ ባቀረበው ዝቅተኛ ዋጋ ይሆናል፡፡
  7. የድርጅቱ ሂሳብ የሚመረመረው የአንድ በጀት አመት ሲሆን አጠቃላይ ፕሮፍይሉን በተመለከተ ከጨረታ ሰነዱ ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘዉ ቅጽ ላይ ዋጋ በመሙላት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ እንደተጠበቀ ነው፡፡
  10. በተጨማሪም ሰነድ ኮፒ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በማያያዝ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 10 ተከታታይ ቀናት ቢሮ ድረስ በመምጣት ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታዉ በ10 ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን አስረኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  • ለበለጠ ማብራሪያ በ ስልክ ቁጥር 09 70 73 1 44 ደዉሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ዜጎች ለዜጎች የልማት ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *