Your cart is currently empty!
የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብ/ አስ /ቡድን ለሁ/እ/እ/ወ/ ጤና ጽ/ቤት የቀራኒዩ ጤና አጠ/ጣቢያ ላይ ለሚገነባው ቀሪ የእናቶች ማረፊያ 1 ብሎክ የተለየዩ ክፍሎችና የእግረኛ መንገድ ሥራ የተቋረጠ እና በሞጣ ከተማ የማህበረሰብ አቀፍ መድሀኒት ቤት ግንባታ፣ የሁ/እ/እ/ወ/ ትምህርት ጽ/ቤት ሥር የገንገርታ ሙሉ ሣይክል ት/ቤት 2 ብሎክ መማሪያ ክፍል ግንባታ የተቋረጠ እና የአጋም ውሀ ሙሉ ሣይክል 1 ብሎክ መማሪያ ክፍል የተቋረጠ የቢሮ ግንባታ፣ የፍትህ ጽ/ቤት የቢሮ ጥገና ማቴሪያል ችሎ እና በወረደው ውስጥ የሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽ/መሣሪያ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት /ለመግዛት ይፈልጋል
Be’kur(Feb 02, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብ/ አስ /ቡድን ለሁ/እ/እ/ወ/ ጤና ጽ/ቤት የቀራኒዩ ጤና አጠ/ጣቢያ ላይ ለሚገነባው ቀሪ የእናቶች ማረፊያ 1 ብሎክ የተለየዩ ክፍሎችና የእግረኛ መንገድ ሥራ የተቋረጠ እና በሞጣ ከተማ የማህበረሰብ አቀፍ መድሀኒት ቤት ግንባታ፣ የሁ/እ/እ/ወ/ ትምህርት ጽ/ቤት ሥር የገንገርታ ሙሉ ሣይክል ት/ቤት 2 ብሎክ መማሪያ ክፍል ግንባታ የተቋረጠ እና የአጋም ውሀ ሙሉ ሣይክል 1 ብሎክ መማሪያ ክፍል የተቋረጠ የቢሮ ግንባታ፣ የፍትህ ጽ/ቤት የቢሮ ጥገና ማቴሪያል ችሎ እና በወረደው ውስጥ የሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽ/መሣሪያ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት /ለመግዛት ይፈልጋል።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
5. የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ለሁሉም የግንባታ ጨረታዎች ለፍትህ ጽ/ቤት የሰነድ መግዥ ዋጋ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ከሁ/እ/እ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ከረዳት ገ/ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የሞሉትን ጥቅል ዋጋ ለግንባታ ለገንገርታ ሙሉ ሣይክል ት/ቤት 2 ብሎክ ግንባታ 220,000 (ሁለት መቶ ሀያ ሽህ ብር)፣ ለአጋም ውሀ ሙሉ ሣይክል ት/ቤት 1 ብሎክ ግንባታ ብር 150,000 (አንድ መቶ ሀምሣ ሽህ ብር)፣ ለማህበረሰብ አቀፍ መድሃኒት ቤት ግንባታ 165,000 (አንድ መቶ ስልሣ አምስት ሸህ ብር) ፣ ለቀራኒዩ ጤና ጣቢያ 1 ብሎክ የእናቶች ማረፊያ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) ግዥዎች፣ የፍትህ ጽ/ቤት የቢሮ ጥገና 60,000 (ስልሣ ሽህ ብር)፣ በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽ/መሣሪያ ግዥ ብር 60,000 (ስልሣ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙከሆነ በሁ/እ/እ/ወ ገንዘብ ጽ/ቤት በገቢ ደረሰኝ ገቢ መደረግ አና ደረሰኙ ከጨረታ ሰነዱ ጋር መያያዝ አለባቸው፡፡
8. አሸናፊው ተጫራች የውል ስምምነት እንዲፈፀም በተገለፀበት ጊዜ ውስጥ ከአሸነፈበት የቢሮ ግንባታ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የግዥ ውል ማስከበሪያ ፕሮፎርማንስ ቦንድ በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ትዕዘዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank grante/ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከአሸናፊው የሚቀርበው የውል ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ ውሉ ከሚጠናቀቅበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 30 ቀናት ጸንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
9. አሸናፊ ግንባታውን ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 25 በመቶ ከማህንዲሱ ግምት ዝቅ ብሎ ካሞላ
- Cost breakdown እና projeket work schedule እንዲሁም በሞላው ዝቅተኛ ዋጋ መስራት የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ /conformation letter/ አሸናፊነት ከተገለጸ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለበት የተጋነነ ዝቅተኛ ሞልተው አሸናፊ ሆነው የግንባታ ተቋራጭ ውል ይዘው ወደ ስራ ሲገቡ ቅድመ ክፍያ አይፈቀድላቸውም፡፡
- የውል ማስከበሪያ የሞላውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የነበረው ተሸሽሎ 25 በመቶ የውል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ግዴታ ይሆናል፡፡
10. የግንባታ የሂሳብ ስሌት በተመለከተ (አርቴሜቲክ ቸክ) በግዥ ፈጻሚ መ/ቤት ባለሙያ ከሚያስተካከለው ውጭ በተጫራቾች በሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና በጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
11. ለግንባታ ለፋይናስ ግምገማ ያለፉ ተጫራቾች ቢያንስ 3 እና በላይ ከሆኑ በጨረታ አከፋፈል ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ ከሂሳብ ስሌት (አርቴሚቲክ ቸክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 2.5 ሁለት ነጥብ አምስት ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ ተጫራቹ ከ3 በታች ከሆነ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት (አርቴሜቲክ ቸክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ አንድ በመቶ ድረስ ብቻ ተቀባይ የሚኖረው ሲሆን ከዚህ በላይ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
12. ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት ኦርጅናል ለብቻው ቅጅውን ለብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሁ/እ/እ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለግንባታ ሥራዎች ለ21 ተከታታይ ቀናት እስከ 22ኛው ቀን 3፡30 እና ለእቃ ግዥ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 16ተኛው ቀን 3.30 ድረስ በማስገባት ተጫራቾች የጫራታ ማወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋና እና ቅጅ ወይም ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ማስገባት ለመ/ቤቱ እና ለተጫራቾች ደህንነት እንደ መወዳደሪያ መስፈርት አይሆንም፡፡
13. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል በቢሮ ቁጥር 4 የጨረታ ጋዜጣው በወጣ በ22 ኛው ቀን 3፡30 ታሽጐ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ የሥራ ቀናት ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይከፈታል፡፡ ለእቃ ግዥ ጨረታው በወጣ 16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጐ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ የሥራ ቀናት ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው የጨረታ መክፈቻ ሰዓት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
16. ውድድሩ በሎት ስለሆነ በአንድ ሎት የተቀመጡትን ዝርዝር ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው፡፡
17. አሸናፊው ውል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ ግንባታውን ስርቶ የሚያጠናቅቅበት ጊዜ ለገንገርታ ሙሉ ሣይክል ት/ቤት 2 ብሎክ ግንባታ 120 ተከታታይ ቀናት ፣ ለአጋም ውሀ ሙሉ ሣይክል ት/ቤት 1 ብሎክ ግንባታ 150 ተከታታይ ቀናት ፣ ለማህበረሰብ አቀፍ መድሃኒት ቤት ግንባታ 120 ተከታታይ ቀናት፣ ለቀራኒዩ ጤና ጣቢያ 1 ብሎክ የእናቶች ማረፊያ 150 ተከታታይ ቀናት፣ ለፍትህ ጽ/ቤት ለቢሮ ጥገና 45 ተከታታይ ቀናት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽ/መሣሪያ ግዥ በ2ዐ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ስርቶ ( ገዝቶ) ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
18. ለግንባታው ሥራ በጨረታው የሚሳተፍ ተጫራቾች ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፡፡
19. ተጫራቾች ለግንባታው የሚጠቀሟቸው የግንባታ ማቴሪያሎች በሙሉ በባለሙያ እየተረጋገጡ ሲያልፍ ለግንባታው ስራ ጥቅም ላይ የሚውሉ ይሆናል፡፡
20. የግንባታው የሚቀርበው አሽዋ ጥራቱን የጠበቀ የአባይ አሽዋ መሆን አለበት፡፡
21. በተጨማሪ በግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽሎ በቀረበው በግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
22. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 661 00 05 ወይም 058 661 19 35 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሁለት እጅ እነሴ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት