የስናን ወረዳ ፍርድ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን የኮምፒዩተር ተዛማጅ እቃዎችን፣ የህንፃ መሳሪያዎችንና የጽዳት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be’kur(Feb 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የስናን ወረዳ ፍርድ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን የኮምፒዩተር ተዛማጅ እቃዎችን፣ የህንፃ መሳሪያዎችንና የጽዳት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  1. በየዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የገበሩ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ምዝገባ ያላቸው፡፡
  4. የእቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሰነድ ከጨረታው ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ዝርዝሩን የያዘውን ሰነድ የማይመለስ ብር 10 (አስር ብር) በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ከእለት ገንዘብ ተቀባይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢንድ ቦንድ) ከሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች ሀሳቡን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ይከፈታል፡፡
  8. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ፣እሁድ እና ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ የውል ዋጋውን 25 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) በማስያዝ ውል መፈረም አለበት፡፡
  10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃ ስናን ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን በሚገኘው ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የሚገዛውን የእቃ ብዛት 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ከጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ማድረግ ከጨረታ ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
  14. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ ለተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  15. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 288 00 64 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡

ማሳሰቢያ:- የጨረታ ውድድሩ በሎት ዋጋ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች እቃውን ማቅረብ ያለባቸው ስ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ስናን ወረዳ ፍ/ቤት