Your cart is currently empty!
የባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት የድርጅት ቤት የጨረታ ማታወቂያ አውጥቷል
Be’kur(Feb 02, 2026)
የጨረታ ማታወቂያ
በአመልካች ወ/ሮ ምንታምር አዝመራው እና በተጠሪ አቶ ሰለሞን አስራት ጌታሁን መካከል ስላለው የባልና ሚስት ክርክር ጉዳይ አቶ ሰለሞን አስራት ስም በቡሬ ከተማ ቀበሌ 02 በምስራቅ እና በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ሐሰን ነጋሽ እንዲሁም በደቡብ አያሌው ፈንታ የሚያዋስነው 1000 ካሬ ሜትር የድርጅት ቦታ ካርታ ቁጥር 8853/2008 የሆነ በመነሻ ዋጋ 18,500,000 (አስራ ስምንት ሚሊየን አምስት መቶ ሺህ ብር) ሆኖ በጨረታ ይሸጣል፡፡ ስለሆነም መጫረት የምትፈልጉ ሁሉ የጨረታ መነሻ ዋጋውን በመያዝ ከጨረታው ቦታ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን የካቲት 26/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ይካሄዳል፡፡ ስለዚህ መጫረት የምትፈልጉ ሁሉ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ንብረቱ ከሚገኝበት ቦታ ቡሬ ከተማ ቀበሌ 02 ድረስ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን አሸናፊው ያሸነፈበትን ¼ ኛውን በሞዴል 85 የሚያስይዝ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት