Your cart is currently empty!
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት የመኖሪያ ቤት የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል
Be’kur(Feb 02, 2026)
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሳሽ አቶ ካሳሁን አዳሙ እና በአፈ/ተከሳሽ እነ አቡየ ቢተው መካከል ባለዉ የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በቲሊሊ ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ ዘለቀ አማረ፣ በምዕራብ ሙሉ ወንድም፣ በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ ጥሩየ ተገኘ መካከል በአቶ ቢተው ዋሲሁን አካል ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 1,267,847 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ስልሳ ሰባት ሺህ ስምንት መቶ አርባ ሰባት ብር ) ይሸጣል፡፡ በመሆኑም በጋዜጣ ማስታወቂያውን ለ30 ተከታታይ ቀን ማለትም ከጥር 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 25/2018 ዓ.ም ድረስ በማዋል የካቲት 26/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 እንዲሸጥ ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ሲመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 ኛውን በሲፒኦ ይዛችሁ መቅረብ አለባችሁ፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት