Your cart is currently empty!
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) የስቱዲዮ ሀ እና ለ ኮንትሮል ሩም የኢንቴረር ስራን ደረጃ 8 ብቻ የማጠናቀቅ (የማስዋብ) ስራ ፈቃድ ያላቸዉን ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ማሰራት ይፈልጋል
Be’kur(Feb 02, 2026)
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 13/2018
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) የስቱዲዮ ሀ እና ለ ኮንትሮል ሩም የኢንቴረር ስራን ደረጃ 8 ብቻ የማጠናቀቅ (የማስዋብ) ስራ ፈቃድ ያላቸዉን ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈለጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የከተማ ልማት የብቃት የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፍኬት፣ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 21 (ሃያ አንድ) ቀናት ከቀኑ 11፡30 ድረስ 500 (አምስት መቶ) ብር በመግዛት አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 106 መግዛት ይቻላል፡፡ የፋይናንስ ኦርጂናልና ኮፒ ሰነዶችን በሁለት ኮፒ በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት ለዚህ ሲባል በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን በ22ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ ፡፡
- ጨረታው በ22ኛዉ ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና
ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡ - የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ ሲፒዩ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት በ22ኛዉ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፤ የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የሚፈለጉትን የኢንቴሪየር ስራ ዓይነት፣ ብዛትና ስፔስፍኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 ድረስ በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
ባህር ዳር