የአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ልዩ ልዩ አገልግሎት ያላቸውን የስራ ክፍሎች እድሳት እና የአጥር እና የጥበቃ ቤት ግንባታ ለማሰራት ደረጃ 7 እና በላይ ያሉ በዘርፉ ህጋዊ የሆኑ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


Be’kur(Feb 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ልዩ ልዩ አገልግሎት ያላቸውን የስራ ክፍሎች እድሳት እና የአጥር እና የጥበቃ ቤት ግንባታ ለማሰራት ደረጃ 7 እና በላይ ያሉ በዘርፉ ህጋዊ የሆኑ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ 

የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡                                                     
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ከመንግስት የሚጠበቅባቸዉን የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የግዥዉ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. የጨረታው ሠነድ ያለምንም ስርዝ ድልዝ መሞላት ይኖርበታል፡፡

3. የተሞላው ዋጋ ቫትን የሚጨምር ወይም የማይጨምር መሆኑ መገለጽ ይኖርበታል፡፡  የተገለጸ ነገር ከሌለው ከቫት ጋር እንደተሞላ ይቆጠራል፡፡

4. ተፈላጊ የሙያ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ  ከደረጃ 7 በላይ ያላቸው፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዛቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከሠነዱ ጋር አብሮ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ታትሞ የሚቆይ ሲሆን በ22ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን በ4፡00 ይከፈታል፡፡

7.  የተዘጋጀውን ሠነድ ቢሮ ቁጥር 09 በአካል በመቅረብ 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡

8. የጨረታው ዝርዝር ጉዳይ በጨረታ መመሪያው ላይ ይገኛል፡፡

9. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

10. ለበለጠ መረጃ በአካል ቢሮ ቁጥር 013 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 27 19/058 220 52 69 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *