የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ አገልግሎት የሚሆን የስብሰባ አዳራሽ ህንፃ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ከሆኑ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ እና ህንፃ ሥራ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል


Be’kur(Feb 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ አገልግሎት የሚሆን የስብሰባ አዳራሽ ህንፃ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ከሆኑ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ እና ህንፃ ሥራ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ሠርቲፊኬት (ቲን) ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚያስረዳ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች ለግንባታ ሥራው በዘመኑ የታደሰ የኮንስትራክሽን የብቃት ማረጋገጫ ደረጃ 5 እና በላይ (Building or General contractor) ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የተጠየቀው የግንባታ ሥራ የማጠናቀቂያ ጊዜ 180 የሥራ ቀናት ነው፡፡
  6. ተጫራቾች ያለፉትን 2 (ሁለት) አመታት ኦዲት የተደረጉ የሀብትና እዳ መግለጫዎች እና ሌሎች የፋይናንስ መግለጫዎችን ተጫራቹ በአሁኑ ወቅት ብቁ የሆነ የፋይናንስ አቋም ያለው መሆኑን እና የረጅም ጊዜ አትራፊነቱን ማሳየት አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች ለዚህ ሥራ ክፍል ባለፉት 5 (አምስት) አመታት ውስጥ የተፈጸመ ወይም በሂደት ላይ ላለ ውል በአመት ውስጥ የተከፈለ በአጠቃላይ የተረጋገጠ ክፍያ አማካይ አመታዊ ሽያጭ /ተርንኦቨር ብር 20,000,000 የሚያንቀሳቀሰ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራች ከዚህ በፊት ላከናወኗቸው ተመሳሳይ ሥራዎች ተያያዥ አገልግሎቶች ከአሠሪው አካል ቢያንስ 1 (አንድ) የመልካም ሥራ ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ አባቸው፡፡ የሚቀርበው ማስረጃም ባለፉት 10 (አስር ) ዓመታት የተሠሩና የበጀት መጠናቸው ቢያንስ 30,000,000 (ሰላሳ ሚሊዬን) መሆን አለበት፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 360,000 (ሶስት መቶ ስልሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያል ተመሰረተ የባንክ ዋስትና በአዊ ብሔረሰብ አስ ተዳደር ገንዘብ መምሪያ ሥም በማዘጋጀት ኦርጅናሉን ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
  10. ተጫራቾች ብቁ ተወዳዳሪ ለመሆን ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 9 ድረስ ያሉት በጨረታ ዝርዝር ሠንጠረዥ እና የጨረታ ቅፆች መነሻ በማድረግ በአባሪ በተያያዘው የጨረታ ማቅረቢያ ሰነድ እና ቅፆች መሰረት ለግምገማ በሚያመች መንገድ ማስረጃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ተጫራቾች በአማርኛ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጥር 25/2018 ዓ.ም ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት 4፡00 ድረስ አዊ/ብሔ/አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ፋይናንስ ቡድን ብር 500 (አም ስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ 
  12. የማወዳደሪያ ሥርዓቱ በሎት ማለትም በጠቅላላ ድምር ውጤት ሲሆን የተቀመጠውን የቴክኒክ መመዘኛ 70 በመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣ እና ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ ይሆናል፡፡
  13.  የግንባታውን ዝርዝር ሥራ (BOQ) እና ዲዛይን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  14. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ቀናት ውስጥ ኦርጅናሉን የመጫረቻ ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥኑ ከሚታሸግበት የመጨረሻ ሰዓት እና ደቂቃ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  15. ጨረታውን የሚያቀርበውና የሚፈርመው ወኪል ከሆነ ከፍ/ቤት የተሰጠውን ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  16. አሸናፊው ተጫራች ያቀረበው ዋጋ ከመሃንዲስ ግምት ወይም ከገበያ ጥናት ከ25 በመቶ ዝቅ ያለ ከሆነ በጨረታዉ የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበዉ ድርጅት ወይም ተቋራጭ ዝርዝር የግንባታ ዋጋ (Cost Breakdown) እና የግንባታ መርሃ-ግብር (Project Work Schedule) እንዲሁም ባቀረበዉ የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ መስራት የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ (Conformation Letter) አሸናፊነቱ በተገለጸ በ5 የሥራ ቀናት ዉስጥ የማቅረብ ግዴታ ያለበት ሲሆን ይህን ማድረግ ካልቻለ ከዉድድር ዉጭ ሆኖ ሁለተኛ የወጣዉ ተጫራች የሞላዉ ዋጋ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነፃጸር የተሻለ ሆኖ ከተገኘ ሥራዉ ለዚሁ ተወዳዳሪ የሚሠጥ ይሆናል፡፡
  17. የሚያስይዙት የዉል ማስከበሪያ በግዥ አፈፃጸም መመሪያ ቁጥር 1/2003 አንቀጽ 14.20 ንኡስ አንቀጽ 3 ሥር ከተፈቀዱ የውል ማስከበሪያ ዓይነቶች ማለትም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ሲፒኦ ጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሚሰላበት የገንዘብ መጠን የጨረታ አሸናፊዉ የሞላውን ጠቅላላ ዋጋ 25 በመቶ የዉል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ግዴታ ይሆናል፡፡
  18. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸው ፊርማቸውና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል መግለጽ አለባቸው፡፡
  19. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡
  20. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዊ/ብሔ/አስ/ገንዘብ መምሪያ በ22 ተኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጐ ከረፋዱ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 22 ተኛው ቀን (የሚከፈትበት ቀን) ብሔራዊ በዓል ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጐ ከረፋዱ 4፡15 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ካልተገኙ የጨረታ ሰነዱ እንዲከፈት ተደርጎ ያልተገኙ ተጫራቾች ግን በእለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  21.  የሚሞላዉ ዋጋ ማንኛዉንም የመንግስት ግብር፣ የትራንስፖርት ወጭና ሌሎች ወጭዎች ካሉ ማካተት ይኖርበታል፡፡
  22. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት የተከለከለ ነው፡፡
  23. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  24. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 227 00 66 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *