የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የተለያዩ ዓይነት የደንብ አልባሳት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 04, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

(ጨረታ ቁጥር ኢአጽ/ግንአዳ/014/2018)

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በበጀት ዓመቱ የሚያሰራጨውን የተለያዩ ዓይነት የደንብ አልባሳት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

.

የደንብ ልብሱ ዓይነት

መለኪያ

ብዛት

1

ውስጥ ልብስ ብትን ጨርቅ

ሜትር

1,440

2

ሻሽ

ቁጥር

320

3

የተለያየ መጠን ያለው የወንዶች ሸሚዝ ቀለም ሰማያዊ ጥቁር ሰማያዊ እና ነጭ

ቁጥር

2,144

4

ጉርድ ቆዳ ጫማ የወንድ 36 ቁጥር ጀምሮ

ቁጥር

1,072

5

ጉርድ ቆዳ ጫማ የሴት 35 ቁጥር ጀምሮ

ቁጥር

320

6

ክራቫት ጥቁር ሰማያዊ ቀለም

ቁጥር

1,600

7

ካልሲ የተለያየ ቀለም

ቁጥር

4,400

8

የደህንነት መከላከያ ጫማ (ሴፍቲ ጫማ)

ቁጥር

500

9

የድርጅቱ ዓርማ (logo) ያለው በአንደኛ ደረጃ ቴትረን 6000 ጨርቅ የተሰፋ ሜንዞ ቱታ (ኮትና ሱሪ ያለው) ቀለም፡ ጥቁር ሰማያዊ ሳይዝ (ልኬት) ሠራተኞችን በመለካት በሚገኝ ልኬት መሠረት የሚሰፋ

ቁጥር

150

10

ጆሮ የሚሸፍን ኮፍያ ቀለም ጥቁር ሰማያዊ የድርጅቱ ዓርማ የሚታተምበት

ቁጥር

200

11

ባርኔጣ (የጥበቃ ኮፍያ) ቀለም ጥቁር ሰማያዊ የድርጅቱ ዓርማ የሚታተምበት

ቁጥር

700

12

የአፍና አፍንጫ መከላከያ ማስክ (Mask)

ቁጥር

150

13

ከቆዳ የተሠራ የእጅ ጓንት

ቁጥር

600

14

የድርጅቱ ዓርማ (logo) ያለው ጋዋን በአንደኛ ደረጃ ቴትረን 6000 ጨርቅ የተሰፋ ቀለም፡ ጥቁር ሰማያዊ እና ነጭ

ቁጥር

1,000

15

ሸርት

ቁጥር

400

16

ፕላስቲክ ቦትስ ጫማ

ቁጥር

300

17

ካፖርት

ቁጥር

300

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

1 በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸውና በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ከድረገጹ (website) አትመው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።

2- ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ፣ የግብር መለያ ሰርተፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።

3- ድርጅቱ ለሚገዛቸው ማንኛውም ዓይነት ጫማዎች የሚወዳደሩት አምራቾች ብቻ ይሆናሉ።

4- ተጫራቾች በከፊል ወይም በሙሉ መጫረት ይችላሉ።

5- ተጫራቾች ከሚጫረቱት አልባሳት ውስጥ ከአንድ እስከ አራት ዓይነት የደንብ ልብስ ለመጫረት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ) እንዲሁም ከአራት ዓይነት በላይ የደንብ አልባሳት ለመጫረት የሚፈልጉ ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (cpo) ወይም ለዘጠና ቀናት የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

6- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

7- ተጫራቾች መወዳደሪያ ሠነዳቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የካቲት 13 ቀን 2018 .. እስከ 800 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንተርፕራይዝ አገልግሎት /ቤት የስብሰባ አዳራሽ በዚሁ እለት ማለትም የካቲት 13 ቀን 2018 .. ከቀኑ 8:45 ይከፈታል።

8- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-551 2400 የውስጥ መስመር 237/262 ወይም በቀጥታ 011-550 4931 መጠየቅ ይቻላል።

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *